አልማዝ አያና በአየር ብክለት በምትናጠው ዴልሂ ድል አድርጋለች

Wednesday, 22 November 2017 12:50

 

ከፍተኛ የአየር ብክለት የተነሳ የህዝቧ ኑሮና ምጣኔ ሀብት በተቃወሰባት የህንዷ ዋና ከተማ ዴልሂ የተካሔደውን የግማሽ ማራቶን ፉክክር በኢትዮጵያውያን አትሌቶች የበላይነት ተጠናቋል። በሴቶች የአለምና የኦሊምፒክ ሻምፒዮኗ አልማዝ አያና ለመጀመሪያ ጊዜ የአደረገችውን የጎዳና ላይ ሩጫ ከአስቸጋሪው የአየር ንብረትጋር በመታገል ድል ማድረጓ አድናቆት አሰጥቷታል።

በቅርቡ የዴልሂ ከተማ ከምንግዜውም የበለጠ የላቀ የተበከለ አየር ንብረት የተመዘገበባት ሲሆን፤ ሯጮች ቀርቶ እግረኞችም ለመተንፈስ የሚቸገሩባት መሆኗ ተዘግቧል። የከተማዋ የህክምና ባለሞያዎች ማህበርም የአየር ንብረቱ ለሩጫ የማይመች መሆን በመግለጽ የዴልሂ ግማሽ ማራቶን ለሌላ ጊዜ እንዲራዘም አሳስቦ ነበር። ይሁንና የሩጫው አዘጋጅ ከከተማው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውድድሩን ማካሔድ እንደሚችል የሚገልጽ ፈቃድ በማግኘቱ ሩጫው በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እሁድ እለት ከ35.000 በላይ ሰዎችን በማሳተፍ ተከናውኗል።

አልማዝ ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረገችው የግማሽ ማራቶን ርቀት ሩጫን 1፡07፡11 በሆነ ሰአት ማጠናቀቅ ችላለች። ሌሎቹ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አባብል የሻነህ እና ነጻነት ጉደታ ሁለተኛና ሶስተኛ ሆነው ገብተዋል።

ከውድድሩ በኋላ አልማዝ አያና በሰጠችው አስተያየት በማሸነፏ ደስታዋን የገለጸች ሲሆን፤ አሯሯጮቹ ከወጡ በኋላ የመሮጫ ቦታው ጠፍቷት ተደናግሯት እንደነበረ ተናግራለች። የተሸለ ሰአት ልታስመዘግብ ትችል እንደነበርም አስታውቃለች።

በተመሳሳይ ርቀት በወንዶች የተካሔደውን ፉክክር ከሁለት አመት በፊት በመድረኩ አሸናፊ የነበረው ኢትዮጵያዊው ብርሃኑ ለገሰ በ59፡46 አሸንፏል። ከአምስት ሰከንድ በኋላም ሌላው ኢትዮጵያዊ አንዳምላክ በልሁ ሁለተኛ ሆኖ ገብቷል። ትውልደ ኬንያዊ አሜሪካዊው ሊኦናርድ ኮሪር ደግሞ ሶስተኛ ሆኗል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
86 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 894 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us