የፌዴሬሽኑ የቅጣት ገቢ በአንድ ወር ውስጥ ግማሽ ሚሊየን ብር ተጠግቷል

Wednesday, 06 December 2017 13:28

 

ስፖርታዊ የስነ ምባግር ጉድለቶችን መቆጣጠርና ማስቀረት የተሳነው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቅጣቶችን የማስተላለፍ አማራጩን እንደቀጠለበት ነው። ይሁንና ፌዴሬሽኑ ቅጣቶችን በማስተላለፉ የስታዲየም ውስጥ ስርአት አልበኝነቶችን መቀነስ አልቻለም። ይልቁንም በየጊዜው ከሚያስላልፋቸው የገንዘብ ቅጣቶች የሚያገኘው ገቢው እየጨመረ ነው።

የዘንድሮው የ2010 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከተጀመረ በአንድ ወር ውስጥ ብቻ ከሜዳ ውስጥ ጥፋቶች ጋር በተያያዘ በክለቦችና ሙያተኞች ላይ ያስላለፈው የገንዘብ ቅጣት ከሩብ ሚሊዮን ብር በላይ ሆኗል። ይህ የገንዘብ መጠን በአመቱ መጨረሻ በሶስትና አራት እጥፍ እንደሚጨምርም መገመት ይቻላል።

በፕሪሚየር ሊጉ አንደኛው ሳምንት ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ከሲዳማ ቡና አቻ በተለያዩበት ጨዋታ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች በጨዋታውና በፌዴሬሽኑ አመራሮች ላይ ስድብ ሰንዝረዋል፤ ቁሶችንም ወርውረዋል በማለት ክለቡ የ80 ሺ ብር ቅጣት ተላልፎበታል። በጨዋታው በሁለት ቢጫ ከሜዳ የወጣው ትርታዬ ደመቀ የ4ሺ ብር እና የ4 ጨዋታ ቅጣት ተጥሎበታል።

ድሬደዋ ከነማም ተመሳሳይ የ80 ሺ ብር ቅጣት የተጣለበት ሲሆን፤ ምክንያቱ ደግሞ በአራተኛ ሳምንት መርሀ ግብ ድሬደዋ ላይ ድሬደዋ ከነማ ከደደቢት ሲጫወቱ በደደቢቱ አጥቂ ጌታነህ ከበደን “ኮከብ ጎል ነጋዴ፤ ኮከብ ጎል ሸማች” እያሉ ዘልፈውታል በሚል ነው።

ወላይታ ድቻ እና ሐዋሳ ከተማ ባደረጉት የአራተኛ ሳምንት ጨዋታ ጨዋታው ለ17 ደቂቃዎች ተቋርጦ የነበረ ሲሆን፤ ለዚህም መንስኤ የሆነው የወላይታ ዲቻ ደጋፊዎች በሐዋሳ ከተማ ደጋፊዎች ላይ ቁስ በመወርወራቸው ነው በሚል ፌዴሬሽኑ በክለቡ ላይ የ70 ሺብር ቅጣት አስተላልፏል። የሐዋሳ ከተማ ክለብ ደግሞ 50ሺብር ተቀጥቷል።

ከዚህ በተጨማሪም በአራተኛው ሳምንት ጨዋታ አዲስ አበባ ስታዲየም ስታዲየም ወልዋሎ ኢትዮ ኤሌትሪክን 3ለ1 በረታበት ጨዋታ በቀጥታ በቀይ ካርድ ከሜዳ የወጣው አዲስ ነጋሽ የ4 ሺ ብር ቅጣትና የ4 ጨዋታ እገዳ ተላልፎበታል። የኢትዮ ኤሌትሪክ ምክትል አሰልጣኙ ኤርሚያስ ተፈራ የ4ሺ ብር ቅጣትና የ5 ጨዋታ እገዳ ተላልፎባቸዋል።

አርባ ምንጭ ከኢትዮ ኤሌትሪክ ባደረጉት የሶስተኛ ሳንት መርሀግብር ደግሞ ከዳኛ እይታ ውጪ ተጫዋች በክርኑ ተማቷል ተብሎ ሪፖርት የቀረበበት የአርባ ምንጭ ከተማ ተጫዋቹ አንድነት አዳነ ተመሳሳይ የ4ሺ ብር ቅጣትና የ4 ጨዋታ እገዳ ተላልፎበታል።

በአጠቃላይም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአራት ሳምንት የፕሪሚይር ሊጉ መርሀግብ ያስተላለፈው የገንዘብ ቅጣት ብቻ 296 ሺ ብር ነው። ከዚህ በተጨማሪም በፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት ጅማ አባ ጅፋር ከሐዋሳ ከነማ ጋር ባካሄዱት ጨዋታ የጅማ አባጅፋር ክለብ ደጋፊዎች “መጥፎ ባህሪ አሳይተዋል” ሲል ፌዴሬሽኑ 100 ሺህ ብር በክለቡ ሊግ ቅጣት አስተላልፏል። በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ 486 ሺህ ብር ከቅጣት በመሰብሰብ የፌዴሬሽኑን የገቢ አቅም አሳድጎለታል። ይህ አሀዝ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በከፍተኛ እጥፍ እንደሚጨምር ይጠበቃል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
75 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 949 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us