የሴካፋ ዋንጫ በዘጠኝ ሀገሮች እየተካሔደ ነው

Wednesday, 06 December 2017 13:30

የሴካፋ ዋንጫ በአፍሪካ አህጉር እድሜ ጠገብ የእግር ኳስ የውድድር መድረክ ቢሆንም በየአመቱ ደረጃው እየወረደ ይገኛል። የተሳታፊ ሀገሮች ዋና ብሔራዊ ቡድናቸውን መላክ ያቆሙ ሲሆን፤ ቁጥራቸውም በየጊዜው እየቀነሰ ነው። ዘንድሮም አስተናጋጇ ኬንያና ተጋባዧ ሊቢያን ጨምሮ ዘጠኝ ሀገሮች ብቻ የሚሳተፉበት ውድድር ሆኗል። ከሊቢያ ጋር በተጋባዥነት ትቀርባለች ተብላ የተጠበቀችው ዙምባብዌ በመጨረሻው ሰአት ላይ አልሳተፍም ማለቷ ታውቋል።

የምስራቅና መካከለኛው ሀገሮች እግር ኳስ ዋንጫ (ሴካፋ) በኬንያ አስተናጋጅነት ባለፈው እሁድ ተጀምሯል። በውድድሩ ላይ ከቀጠናው አባል ሀገሮች ስምንት ብቻ የሚሳተፉ ሲሆን፤ የሰሜን አፍሪካዊ ሊቢያ በተጋባዥት የቀረበች ብቸኛዋ ሀገር ናት። ሌላዋ ተጋባዥ ሀገር ዙምባብዌ በመጨረሻዎቹ ቀናት ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ስጋቷን በመግለጽ እንደማትሳተፍ አሳውቃ ቀርታለች።

የሴካፋ ዋንጫ በየጊዜው የጥራት ደረጃው እየወረደ መገኘቱ እያስተቸው ነው። ውድድሩ ከነጭራሹ ቢቀር የተሻለ እንደሆነም አስተያየት የሚሰጡ ወገኖች እየበዙ ነው። በአንጻሩ ደግሞ ውድድሩ ከሚቀር ለወጣቶች ልምድ ማግኛ የውድድር መድረክ ሆኖ ቢቀጥል ጥሩ ነው የሚሉም ወገኖች አሉ።

ከቅርብ አመታት ወዲህም ተሳታፊ ሀገሮች ዋና ቡድናቸውን መላክ ትተዋል። ኢትዮጵያም ለዘንድሮው የውድድር መድረክ ጥቂት ልምድ ያላቸው ተጫዋቾችን ከብዙ አዳዲስ ልጆች ጋር የተዋቀረ ቡድኗን ነው የላከችው።

በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ የሚመራው የኢትዮጵያ የሴካፋ ቡድን ከአዲሲቷ የአፍሪካ ሀገር ደቡብ ሱዳን፣ ብሩንዲና ዩጋንዳ ጋር ነው የተመደበው። የመጀመሪያ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታውን ማክሰኞ እለት ከደቡብ ሱዳን ጋር ያደረገ ሲሆን፤ ሁለተኛ ጨዋታውን የፊታችን ሐሙስ ቀን ከብሩንዲ ጋር ያከናውናል። እሁድ ደግሞ የመጨረሻውንና ሶስተኛውን የምድብ ማጣሪያ ጨዋታውን ካለፈው የሴካፋ ዋንጫ አሸናፉ ዩጋንዳ ጋር ያደርጋል።

አሰልጣኝ አሸናፊ ወደ ኬንያ ከመጓዛቸው በፊት በሰጡት አስተያየት በውድድሩ ጥሩ ልምድ ለማግኘት ወደ ስፍራው እንደሚሄዱ ነው የተናገሩት። በአንጻሩ ደግሞ የቡድኑ ተጫዋቾች ዋንጫ የማምጣት ፍላጎት እንዳቸው ነው በተለያዩ የሀገር ቤት መገናኛ ብዙሀን ሲናገሩ የተሰሙት።

ደካማ የእግር ኳስ ደረጃ ያላቸው ሀገሮች በሚወዳደሩበት መድረክ አሰልጣኝ አሸናፊ ልምድ የማግኘት እቅድ መያዛቸው የሚያስገርም ሆኗል። የቡድኑ ተጫዋቾች ግን ከአሰልጣኙ በተቃራኒ ሴካፋን ዋንጫ ይዘው ለመመለስ ነው የተዘጋጁት።

የ2017 የቻን ውድድር የማዘጋጀት እድሏን የተነጠቀችው ኬንያ የሴካፋ ዋንጫን በማዘጋጀት አቅሟን ለማሳየት እንደምትጥር ይጠበቃል። ብሔራዊ ቡድኗም ዋንጫውን በማስቀረት ደጋፊዎቹን ለማስደሰት ነው የተዘጋጀው። የሀራምቤ ኮከቦች በመጀመሪያ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታቸው ርዋንዳን  2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈው ጉዟቸውን በድል የጀመሩ ሲሆን፤ እስከ ፍጻሜው ጨዋታ እንደሚደርሱ ተገምተዋል።

ኢትዮጵያ ያለፈውን የ2015 የሴካፋ ዋንጫን አዘጋጅታ ሶስተኛ ደረጃ ማጠናቀቋ የሚታወስ ሲሆን፤ ከዚህ በፊት የውድድሩን ዋንጫ አራት ጊዜ ማንሳቷ ይታወሳል።

የሴካፋ ዋጫን በብዛት በማሸነፍ ዩጋንዳ 14 ጊዜ አሸናፊነት ክብረወሰኑን የያዘች ሀገር ስትሆን፤ ኬንያ ስድስት ጊዜ ዋንጫውን በማንሳት ከዩጋንዳ ቀጥሎ የምትጠቀስ ሀገር ናት።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
91 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1038 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us