ኢትዮጵያ ከሴካፋ ዋንጫ በጊዜ ተሰናብታለች

Wednesday, 13 December 2017 13:06

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምስራቅና መካከለኛው የአፍሪካ ሀገሮች ዋንጫ (ሴካፋ) በተሳትፎ ታሪኩ አስከፊ የሚባል ሽንፈትን አስተናግዷል። በውድድር መድረኩ በምድብ ማጣሪያው በጊዜ ተሰናባች ከሆኑ ሀገሮችም አንዱ ሆኗል። አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ለሽንፈታቸው የሚሰጡት ምክንያት ደግሞ የስፖር ቤተሰቡን የሚያስቆጣ ሆኗል።


ኬንያ እያስተናገደች በሚገኘው በዘንሮው የሴካፋ ዋንጫ ተጋባዧ ሊቢያን ጨምሮ ዘጠኝ ሀገሮች በሁለት ምድብ ተከፍለው እንዲወዳደሩ ተደርጓል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከደቡብ ሱዳን፣ ብሩንዲና ኡጋንዳ ጋር ነበር የተመደበው።


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ደካማ በሚባለው የውድድር መድረክ በመጀመሪያው የምድብ ማጣሪያ ጨዋታም ደቡብ ሱዳንን 3ለ0 አሸንፎ ነበር። ውጤቱም በቀጣይ ጨዋታዎች ቡድኑ ከፍተኛ ግምት እንዲሰጠው አድርጎ ነበር።


በቀጣዩ የምድብ ማጣሪያ ከብሩንዲ ጋር በአደረገው ጨዋታ ግን ቡድኑ አቅም አልባ ሆኖ ታይቷል። በመጀመሪያው አጋማሽ ያስቆጠረውን አንድ ግብ ማስጠበቅ ሳይችል ቀርቷል። በጨዋታው አራት ግቦችን አስተናግዶ 4ለ1 ተሸንፏል። በጨዋታው ብሩንዲዎች አራት ግብ ሊሆኑ የሚቸሉ ሙከራዎችን በማምከናቸው እንጂ ቡድኑ ከአራት በላይ ግቦችን ያስተናግድ እንደነበር ታይቷል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሰፊ የግብ ልዩነት መሸነፉ ብቻ ሳይሆን በጨዋታ እንቅስቃሴም በተጋጣሚው መበለጡ ሽንፈቱን አስከፊ አድርጎታል። ብሩንዲም ኢትዮጵያን ለመጀመሪያ ጊዜ በማሸነፍ አዲስ የድል ታሪክ ያስመዘገበችበት ሆኗል።


በመጨረሻው የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ኡጋዳን የገጠመው የአሰልጣኝ አሸናፊ ቡድን በሰፊ የግብ ልዩነት ሊሸነፍ እንደሚችል ተገምቶ ነበር። ጨዋታው ከውድድሩ የሚኖረውን እጣ ፈንታ የሚወስን በመሆኑ የኢትዮጵያ ቡድን የኡጋንዳን ጫና ተቀቋቁሞ ሲጫወት ታይቷል። ከእረፍት በፊት በ22ኛው ደቂቃ በአቡበከር ሳኒ አማካኝነት ግብ በማስቆጠር መምራት ችሎም ነበር። ውጤቱ በስድስት ነጥብ ከምድቡ እንዲያልፍ የሚያደርገው ነበር። ይሁንና ጨዋታው ሊጠናቀቅ አስር ደቂቃዎች ሲቀሩ ኡጋንዳዎች አንድ ግብ አስቆጥረው አቻ መሆ ችለዋል። ጨዋታው በእኩል 1ለ1 በመጠናቀቁም ኡጋንዳ ነጥቧ አምስት በማድረግ ከኢትዮጵያ የበላይ በመሆን ወደ ቀጣዩ ዙር አላፊነቷን አረጋግጣለች።


የኢትዮጵያ ቡድን በውድድሩ ለመቆየት ሰኞ እለት የብሩንዲና ደቡብ ሱዳን ጨዋታ ውጤትን መጠበቅ ብቻ ነበር። በጨዋታውም ደቡብ ሱዳን ብሩንዲን ከአራት ግብ በላይ በማስቆጠር ካሸነፈች ብቻ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ጠባብ እድል ነበረው። ይሁንና ሰኞ እለት ከደቡብ ሱዳን ያለግብ የተለያየችው ብሩንዲ ነጥቧን አምስት በማድረስ ኡጋንዳን ተከትላ ወደ ቀጣዩ ዙር ሀላፊ መሆኗን አረጋግጣለች። ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳንም ተሰናባች ሆነዋል።


‹‹ልምድ ለማግኘት ነው የምንሔደው›› ሲሉ ከውድድሩ በፊት ተናግረው የነበሩት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ አሸናፊ ቡድናቸው ከሽንፈት ያገኘው ልምድ ምን እንደሆነ ለማወቅ ይከብዳል።


ከብሩንዲው የ4ለ1 ሽንፈት በኋላ ተጫዋቾቼ ልምድ የሌላቸው ስለሆኑ ነው ሲሉ ለሽንፈታቸው ምክንያት ተናግረው ነበር። በአበባው ቡጣቆ አምበልነት የሚመራው ብሔራዊ ቡድኑ ግን አሰልጣኙ ባሉት ደረጃ ልምድ የሌላቸው ተጫዋቾች ስብስብ አይደለም። ከተለያዩ ክለቦች የተውጣጡ ልምድ ያላቸውና ለብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠሩ ጥቂት ተጫዋቾቾን ያካተተ ነበር። ብዙዎቹ ልምድ የላቸውም የሚባሉ አይደሉም።


ብሔራዊ ቡድን ከተረከቡ በኋላ ተደጋጋሚ ሽንፈት ያስተናገዱት አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ከሴካፋ ዋንጫ በጊዜ መሰናበቱ ጠንካራ ትችት እንዲሰነዘርባቸው አድርጓል። አሰልጣኙ ለሽንፈታቸው የሚሰጡት ምክንያት ደግሞ ተአማኒነት የሌለውና የስፖርት ቤተሰቡን የሚያበሳጭ ነው። አሰልጣኙ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር የሚኖራቸው ቆይታ በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
68 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 98 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us