የማራዶና ሀውልት በህንድ ይፋ ሆኗል

Wednesday, 13 December 2017 12:20

 

በአለም የእግር ኳስ ታሪክ ውስጥ አይረሴ ታሪክ መጻፍ የቻለው አርጀንቲናዊው ዲያጎ አርማዶ ማራዶና አሁንም ድረስ ተወዳጅነቱ አልቀነሰም። በህንድ የተሰራለት ሀውልት በተመረቀበት ወቅትም የከተማዋ ነዋሪዎች በብዛት በመውጣት ደማቅ አቀባበል አድርገውለታል። ስሙን እየጠሩ በማሞገስም ዘምረውለታል።


ህንድ በእግር ኳስ ስፖርት የገነነ ስምና ታሪክ ባይኖራትም ለአለማችን ድንቅ ተጫዋች ማራዶና ግን ያላትን ከፍተኛ ፍቅር ለመግለጽ በምስሉ ሀውልት አሰርታ አቁማለታለች። ሀውልቱንም ራሱ ማራዶና በተገኘበት እንዲመረቅ አድርጋለች።


ማራዶና ህንድ ዴልሂ ሲገባ የሀገሪቱን የባህል ልብስ ለብሶና ግንበሩ መሀል ላይም ቀይ ቀለም ተቀብቶ ታይቷል። 12 ጫማ ርዝመት ያለውና የ1986 የአለም ዋንጫን ሲያሸንፍ የተቀበለው ዋንጫን በእጁ ይዞ የሚታይበት ሀውልቱን መርቋል።


ህንዳውያን ለክብሩ ሀውልት ማሰራታቸው እጅጉን እንዳስደሰተው ተናግሯል። ሀገሪቱ እግር ኳስ ተወዳጅ ስፖርት እንዲሆን እያደረገች ያለውን ጥረት አድንቆ እርሱም የሚችለውን ሁሉ በማድረግ እንደሚያግዝ ቃል ገብቷል።


በህንድ በሚኖረው ቆይታ የተለያዩ ታሪካዊ ቦታዎችን የሚጎበኝ ሲሆን፤ በሀገሪቱ ተወዳጅ የሆነውን ስፖርት የክሪኬት ጨዋታዎችንም በስታዲየም ተገኝቶ እንደሚከታተል ታውቋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
81 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 102 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us