መሀመድ ሳላህ የቢቢሲ የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋች ተብሏል

Wednesday, 13 December 2017 13:12


ግብጻዊው የሊቨርፑል የፊት መስመር ተጫዋች መሀመድ ሳላህ የ2017 የቢቢሲ ኮከብ አፍሪካ ተጫዋች ሽልማትን ማሸነፍ ችሏል። በአጭር ጊዜ ውስጥ በሊቨርፑሉ ክለብ ተጽዕኖ ፈጣሪ በመሆን ቡድኑን ውጤታማ እያደረገ ነው።


የ25 አመቱ አጥቂ በ2014 ለቼልሲ ክለብ በመፈረም የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን መቀላቀሉ ይታወሳል። በቼልሲ ቤት ውጤታማ ጊዜን ማሳለፍ ባይችልም ሌላኛው የፕሪሚየር ሊጉ ክለብ ሊቨርፑል እንዳዛወረው ይታወሳል።


መሐመድ ሳላህ በሎቨርፑል ክለብ ከአሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ጋር መስራት ከጀመረ በኋላ ተጨዋቹ ስኬታማ የውድድር ጊዜ እያሳለፈ ይገኛል። ለቀይ ለባሾቹ ክለብ ወሳኝ ግቦችን በማስቆጠርም ለቡድኑ ውጤታማት የላቀ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ከዚህ በተጨማሪም ሀገሩ ግብጽ ከ1990 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአለም ዋንጫ መድረክ እንድታልፍ ቁልፍ ሚና ነበረው። ግብጽ በአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ እንድትቀርብም ግቦችን በማስቆጠር የጎላ ድርሻ ነበረው። በአጠቃላይም በ2017 ከክለቡና ከሀገሩ ብሔራዊ ቡድን ጋር ምርጥ ብቃት በማሳየቱ የቢቢሲ ኮከብ ተጫዋች ሽልማትን እንያሸንፍ አስችሎታል።


በዘንድሮው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መሐመድ ሳላህ በ16 ጨዋታዎች 13 ግቦችን በማስቆጠር የኮከብ ግብ አግቢነቱን ፉክክር እየመራ ይገኛል። ለግብጽ ብሔራዊ ቡድን ለ2018 የአለም ዋንጫ እንድታልፍ ያደረጋትን ወሳኝ ግብ በማስቆጠር ስሙን በታሪክ መዝገብ ማጻፍ ችሏል።


ተጫዋቹ ሰኞ እለት የቢቢሲን የአፍሪካ ምርጥ ተጫዋች ሽልማት ካሸነፈ በኋላ በሰጠው ሽልማቱ በአመቱ ውስጥ ያሳየው አቋም ምርጥ እንደነበር የሚመሰክር በመሆኑ ደስተኛ ነኝ ብሏል። በቀጣይ አመታትም ምርጥ ብቃቱን በእግር ኳስ ጨዋታዎች ላይ ለማሳየት እንደሚዘጋጅ አስታውቋል። ከዚህ በተጨማሪም የግብጽ የምንግዜም ምርጥ ተጫዋች መሆን እንደሚፈልግም ተናግራል።


ባለፈው አመት ሽልማቱን አልጄሪያዊው የሌስተር ሲቲ አጥቂ ሪያድ ማህሬዝ ማሸነፉ ይታወሳል። ዘንድሮ ከመሐመድ ሳላህ ጋር የጋቦኑ ፒየር አቡሜያንግ እና የሴኔጋሉ ሳዲዮ ማኔ በእጩነት ቀርበው እንደነበር ይታወሳል።


ከዚህ በፊት የቢቢሲ የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋች ሽልማትን ከመሀመድ ሳላህ በፊት የወሰዱ ግብጻውያን ተጫዋቾች መሀመድ ባራካት በ2005 እና መሀመድ አቡታሪካ በ2008 ናቸው።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
183 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1074 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us