ሮናልዶ የአለም ምርጡ ተጨዋች እኔ ነኝ

Wednesday, 13 December 2017 13:15

 

ፖርቱጋላዊው የሪያል ማድሪድ ተጫዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሰሞኑን ለአምስተኛ ጊዜ የአለማችን ኮከብ ተጫዋች ሽልማትን መውሰዱ ይታወቃል። የ32 አመቱ አጥቂ ከቅርብ ተፎካካሪው ሊዮኔል ሜሲ እኩል መጋራቱ ባሻገር ከሽልማቱ በኋላ የሰጠው አስተያየት አነጋጋሪ አድርጎታል። ‹‹እንደኔ ያለ ተጫዋች ታይቶም አይታወቅ›› ሲል ከዘመናችን ተጫዋቾች ሁሉ እርሱ ልዩ መሆኑን በአንደበቱ መስክሯል።


“ከሌሎች ተጫዋቾች ጋር ማነጻጸራቸውን አከብራለሁ። ነገር ግን ከእኔ የተሻለ ተጫዋች ፈጸሞ አላውቅም። ይህንን ሁልጊዜም ነው የማስበው። እኔ የሰራሁትን ታሪክ ማንኛውም ተጫዋች ሰርቶ አውቅም። ከእኔ የበለጠ የተሟላ እግር ኳስ ተጫዋች የለም። በሁለቱም እግሮቼ እጫወታለሁ፣ ፈጣን ነኝ፣ ጥሩ ጉልበት አለኝ፤ በጭንቅላት ኳስም በጣም ጥሩ ነኝ፤ ግቦችን አስቆጥራሁ፤ ሌሎች ተጫዋች ግብ እንዲያስቆጥሩም ምቹ ኳሶችን አቀብላለሁ።” በማለት ከሌሎች ተጫዋች የተለየ የሚያደርጉት ብቃቶቹን ዘርዝሯል።


‹‹ከእኔ የበለጠ ሜሲን ወይም ኔይማርን የሚያስበልጡ ሰዎች አሉ። ነገር ግን እውነቱን ነው የምነግራቹ ማናቸውም ቢሆኑ ከእኔ የበለጠ ምሉዕ ተጫዋች አይደሉም። ማንም ተጫዋች እንደ እኔ የተናጥል ሽልማቶችን የወሰደ የለም። የምናገረው ስለ ባሎን ደኦርን አይደለም። እሱም ቢሆን አንዳች ነገር ይመሰክራል። ስኬታማ የሆንኩት አንዳንዶች እንደሚያስቡት ጂም ውስጥ በምሰራው ስራ ብቻ አይደለም። የብዙ ነገሮች ድምር ውጤት ነው። እንደ ሌብሮን ጀምስ ወይም ፍሎይድ ሜይዌዘር ያሉ ሌጀንዶች የተሟሉ ስፖርተኞች የሆኑት በእድል ወይም በአጋጣሚ አይደለም። ብዙ ነገሮች ተዋደው ነው። ከሀሉም የላቀ ስፖርተኛ ለመሆንና በስኬት ለመቆየት ከሌሎች የበለጠ ተሰጥኦ ሊኖርህ ይገባል።›› በማትም ተናግሯል።


ይህ የሮናልዶ አስተያየት ደጋፊዎቹ ቢስማሙበትም በበርካቶች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል። አሁንም እርሱን ከሜሲ ጋር ማነጻጸሩ እንዲቀጥል አድርጓል።


‹‹ሰባት የባሎን ደ ኦር ሽልማትና ሰባት ልጆች እንዲኖሩኝ እፈልጋለሁ›› ሲል የተደመጠው ሮናልዶ፤ በቀጣዮቹ አመታትም በምርጥ ተጨዋችነት ለመገኘት ጠንክሮ እንደሚሰራ አስታውቋል። በሪያል ማድሪድ ቤት ደስተኛ እንደሆነ በመግለጽም ወደ ሌላ ክለብ ሊዛወር ነው የሚሉ ዘገባዎችን አስተባብሏል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
133 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1076 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us