የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ታላቁ ሩጫ በሐዋሳ ተካሔደ

Wednesday, 20 December 2017 13:06

 

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰረተበትን 75ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው የጎዳና ላይ ህዝባዊ የሩጫ መድረክ በሐዋሳ ከተማ ተካሔደ። በቀጣዮቹ ሳምንታትም ተመሳሳይ የሩጫ መድረኮች በሌሎች አራት ከተሞች ይካሔዳሉ።

የጎዳና ላይ የሩጫ መድረክ ባለፈው እሁድ ቀን በሐዋሳ ከተማ በድምቀት ተከናውኗል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ያዘጋጁት የ7 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ይሸፍናል  ‹‹የኔ ባንክ፤ የኔ ኩራት›› በሚል መሪ ቃል የተካሔደው የሩጫ መድረኩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 75ኛ አመት በአልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ነበር። ከሶስት ሺ በላይ የከተማው ህዝብ የተሳተፉበትን ሩጫ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ፣ የደቡብ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና የ800 ሜትር ሯጯ አትሌት ፋንቱ ሚጌሶ አስጀምረውታል። በአትሌቶች መካከልም ጠንካራ ፉክክር ተካሐዷል።

ከዚህ በተጨማሪም የሩጫው መድረክ እድሜያቸው 75 አመት በሞላቸው አዛውንቶች መካከል የ500 ሜትር ፉክክርንም ያስናተገደ ነበር። የሐዋሳ ከተማ በተለያዩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ቢሮዎች በሚሰሩ ሰራተኞች መካከልም ፉክክር ተደርጓል።

በአትሌቶች መካከል የተካሔደው ፉክክር በሁለቱም ጾታ ጠንካራ ፉክክር የተስተዋለበት ሲሆን፤ በሴቶች ይታይሽ፤ በወንዶች ደግሞ ጥላሁን ሀይሌ አሸንፈዋል። በሁሉቱም ጾታ አሸናፊ ለሆኑ አትሌቶች የዋንጫና የ10ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ባንኩ አምስት ባለእድለኛ ለሆኑ ተሳታፊዎች በመረጡት የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቦታ የደርሶ መልስ የአውሮፕላን ትኬትና የአምስት ቀን የሆቴል ወጪ ተሸፍኖላቸው እንዲዝናኑ የሚያደርግ የዕጣ ስጦታ አግኝተዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ የሩጫ መድረኩ በቀጣይ በመቀሌ፤ ባህርዳርና አዳማ ከተሞች ላይ የሚከናወን ሲሆን፤ የመጨረሻውና የማጠቃለያው መድረክ በአዲስ አበባ ይከናወናል። በሁለቱም ጾታ አጠቃላይ የአሸናፊዎች አሸናፊ ለሚሆኑ አትሌቶች የ75ሺህ ብር ሽልማት ማዘጋጀቱ ታውቋል።

የባንኩ 75ኛ ዓመት በአል ዝግጅት ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ኤፍሬም መኩሪያ እንደገለጹልንም ባንኩ የህዝብ እንደመሆኑ መጠን ክብረ በአሉን ከህዝብ ጋር ለማክበር አስፈላጊ ሆኗል። ከዚህ በተጨማሪም መድረኩ ከባንኩ ጋር አብረው የዘለቁትን ለማመስገንና በቀጣይም በደንበኝነት እንዲቆዩ ለማስቻል የሚረዳ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኢትዮጵያ ስፖርት በተለይም በአትሌቲክስ እንደ መሰረት ደፋር ያሉ ውጤታማ ስፖርተኞችን ያፈራ የአትሌቲክስ ክለብና የእግር ኳስ ክለቦችን በማቋቋም ስፖርትን የመደገፍ ልምድ አለው። የወንዶቹ የእግር ኳስ ቡድን ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በመውረዱና እንደተጠበቀው ውጤታማ ባለመሆኑ ቢፈርስም ለብሔራዊ ቡድንም የሚጫወቱ ልጆች ያሉበት የሴቶች ቡድኑ በውድድር ላይ ይገኛል።

ባንኩ ከእግር ኳስና አትሌቲክስ በተጨማሪ በሌሎች የስፖርት አይነቶችም ውጤታማ ስፖርተኞች ለማፍራት እንደሚሰራ አቶ ኤፍሬም ገልጸዋል። ዋናውን የታላቁ ሩጫ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫን በዋና ስፖንሰርነት መሆን በማስታወስ ህዝባዊ የስፖርት መደገፋቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
95 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 704 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us