ቀነኒሳ በቀለ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል

Wednesday, 20 December 2017 13:12

 

ለረጅም ወራት በጉዳት ከወድድር መድረኮች የራቀው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ወደ አሸናፊነት የመለሰውን ውጤት አስመዝግቧል። በማራቶን የአለም ክብረወሰን የማሻሻል እቅዱን ለማሳካት መዘጋጀቱንም አስታውቋል።

ከለንደኑ የአለም ሻምፒዮና የቀረውና ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶት በነበረው የዘንድሮው የበርሊን ማራቶን ፉክክርም አቋርጦ የወጣው ቀነኒሳ ዳግም ወደ ውድድር  ተመልሷል። የ2017 የውድር አመት ከማብቃቱ በፊትም ድል ያደረገበትን ውጤት በህንድ አስመዝግቧል።

ባለፈው እሁድ በህንድ ኮልካታ ከተማ በተካሔደ የ25 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ቀነኒሳ የቦታውን አዲስ ክብረወሰን በማሻሻል ጭምር ነበር ያሸነፈው። ርቀቱንም በ1፡13፡ 48 ሰአት ያጠናቀቀ ሲሆን፤ እሱን በመከተል ኤርትራዊው ጸጋይ ጥኡማይ በ1፡14፡21 ሁለተኛ ሆኗል።

በሴቶች መካከል የተካሔደውን ፉክክር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ደጊቱ አዝመራው ርቀቱን በ1፡26፡01 በማጠናቀቅ አሸንፋለች።

በትራክ ላይ የሯጭነት ዘመኑ ስኬታማ የነበረው የአለምና የኦሊምፒክ ሻምፒዮኑ ቀነኒሳ የ5.000 እና 10.000 ሜትር ርቀቶች የአለም ክብረወሰኖች በስሙ ይገኛሉ። በማራቶን ሩጫም ተመሳሳይ ስኬት ማሰመዝገብ ይፈልጋል። በበርሊን ማራቶን ያስመዘገበው 2፡03፡03 ሰአት ሁለተኛው የርቀቱ ፈጣን ሰአት ነው። ይህንን ሰአት እንደሚያሻሻለውም በልበ ሙሉነት ተናግሯል። በ2020 የቶኪዮ ኦሊምፒክ በማራቶን መሮጥ ፍላጎት እንዳለው መናገሩን የህንዱ ሂንዱታይምስ ጋዜጣ ዘግቧል።

በ2014 የተመዘገበው የማራቶን የአለም ክብረወሰን 2፡02፡57 በኬንያዊው ዴኒስ ኪሜቶ በርሊን ላይ እንደተመዘገበ ይታወሳል። በቀጣዩ የ2018 ለንደን ማራቶን የሚሳተፈው ቀነኒሳ የርቀቱን ክብረወሰን ለማሻሻል እንደሚሮጥ አስታውቋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
82 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 201 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us