ለአፍሪካ ኮከብ ተጫዋች ሽልማት ሦስቱ ዕጩዎች ታውቀዋል

Wednesday, 20 December 2017 13:14

 

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ለ2017 የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋች ሽልማት የታጩ የመጨረሻቹን ሶስት እጩዎች ይፋ አድርጓል። ሁለቱ የሊቨርፑል ክለብ አጥቂዎች ግብጻዊው መሀመድ ሳላህ እና ሴኔጋላዊው ሳዲዮ ማኔ ለ2017 የካፍ ኮከብ ተጫዋችነት ሽልማት ከጋቦኑ አባሜያንግ ጋር ታጭተዋል።

ከሶስቱ እጩዎች መካከልም ዘንድሮ ከሊቨርፑል ጋር ድንቅ ብቃት ላይ የሚገኘው ግብጻዊው አጥቂ መሐመድ ሳላህ ለሽልማቱ የተሻለ እድል እንዳለው ታምኗል። ተጨዋቹ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በኮከብ ግብ አግቢነት እየመራ ይገኛል። ግብጽ ለ2018 የአለም ዋንጫ እንድታልፍም ቁልፍ ሚና ከነበራቸው ተጫዋቾች መካከል አንደኛው ነው። መሐመድ ሳላህ ባለፈው ሳምንት የቢቢሲን የ2017 የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋች ሽልማት ማሸነፉ ይታወሳል።

ሌላኛው የሊቨርፑል አጥቂ ሴኔጋላዊው ሳዲዮ ማኔ በእንግሊዙ ክለብ ድንቅ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን፤ ግቦችን በማስቆጠር እና የተመቻቹ ኳሶችን በማቀበል አድናቆትን አግኝቷል። በሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ውስጥም የላቀ አስተዋጽኦ ያለው የፊት መስመር አጥቂ ነው።

በዘንድሮው የካፍ ኮከብ ተጫዋች ሽልማት የመጨረሻዎቹ ሶስት እጩዎች ውስጥ የተካተተው የጋቦኑ ፒየር ኤምሪክ አባሜያንግ ከሁለት አመት በፊት ሽልማቱን መውሰዱ ይታወሳል። ተጨዋቹ በጀርመኑ ክለብ ቦርሲያ ዶርትሙንድ ግቦችን በማቆጠር ከቡንደስሊጋው ኮከቦች ውስጥ የሚጠቀስ ነው።

የካፍ የ2017 የኮከብ ተጫዋች ሽልማት በፈረንጆቹ ጃንቀ ዋሪ 4 ቀን 2018 በጋና አክራ ከተማ በሚከናወን ስነ ስርአት ይፋ ይሆናል። በእለቱም ከወንዶችና ከሴቶች ኮከብ ተጫዋቾቸ በተጨማሪ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝና ብሔራዊ ቡድን እንዲሁም ምርጥ የአፍሪካ ክለብ ምርጫም ይከናወናል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
88 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 242 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us