የፌዴሬሽኑ አመራር ምርጫ በውዝግቦች እንደታጀበ በጥር ወር ይካሔዳል

Wednesday, 27 December 2017 12:50

 

በተለያዩ ምክንያቶች እየተራዘመ ቆይቶ ለታህሳስ 16 ቀን ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአመራር ምርጫ ሌላ ተለዋጭ ቀን ተቆርጦለታል። በቀጣዮቹ ቀናትም አስገዳጅ ሁኔታዎች ካልተፈጠሩ በስተቀር በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ጥር 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ይካሔዳል ተብሏል።

በውዝግቦች የታጀበው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫ መፍትሄዎችን ሳያስተናግድ እንዲካሔድ መወሰኑ ቅሬታዎችን ፈጥሯል። የምርጫ ውጤቱ ተቀባይነትም ጥያቄ ውስጥ እንዲወድቅ አድርጓል። የእጩዎች ተገቢነትና የአስመራጭ ኮሚቴው ገለልተኛነት አሁንም ምላሽ ያለገኙ የውዝግብ ምክንያቶች ናቸው። ውዝግቦቹን ለመፍታት የሚችሉ ህግና መመሪያ እንዲሁም ብሔራዊ ተቋም አቅም ደካማ መሆን ለችግሮቹ መባባስ ጉልህ አስተዋጽኦ አድርጓል።

ገለልተኛነቱ ጥያቄ የበዛበት የአስመራጭ ኮሚቴው ለፕሬዝዳንትነት የሚወዳደሩ አምስት እጩዎችንና 16 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት የሚወዳደሩ እጩዎችን ተቀብሎ ማጽደቁ ይታወሳል። ለፕሬዝዳንትነት ከቀረቡት እጩዎች መካከልም የደቡብ ክልልን በወከሉት ዶክተር አሽብር ወልደጊዮርጊስ ህጋዊነት ላይ ሶስት ክልሎች ቅሬታ እንዳላቸው አስታውቀዋል። ዶክተሩ የቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆነው በተመረጡበት አመት ለሌላ ፌዴሬሽን ለመመረጥ መወዳደር እንደማይችሉም ክልሎቹ በመጥቀስ እጩነታቸው እንዲሰረዝ ጠይቀው ነበር።

ይሁንና አስራጭ ኮሚቴው በአብላጫ ደምጽ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት ዶክተሩ ለመወዳደር የሚከለክላቸው ህግ እንደለሌለ በመጥቀስ እጩነታቸውን አጽድቋል። ይህ ውሳኔ ተገቢ አይደለም ሲሉ ቅሬታ አቅራቢዎቹ በድጋሚ ይግባኝ ጠይቀው ነበር። ይሁንና የቅሬታ አቅራቢዎቹ የይግባኝ ጥያቄ ሲቀርብ የይግባኝ ማቅረቢያ ቀነ ገደቡ በማለፉ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። ይሁንና ቅሬታ አቅራቢዎቹ ክልሎች እስከመጨረሻው ጊዜ ድረስ ተቃውሟቸውን በማሰማት እንደሚታገሉ አስታውቀዋል።

ለፕሬዝዳንትነት ከዶክተር አሸብር በተጨማሪ አቶ ተካ አስፋው ከአማራ ክልል፤ አቶ ጁነዲን ባሻ ከድሬደዋ ከፍተኛ ተፎካካሪ ሆነው የቀረቡ እጩዎች ናቸው። የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች የነበረው አንተነህ ፈለቀን ውክልና ያነሳው የኦሮሚያ ክልልና ጋምቤላም ለፕሬዝዳንትነት ቦታው ተወካዮቻቸውን ማቅረባቸው ይታወሳል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
67 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 268 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us