አሰልጣኝ አሸናፊ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ኢትዮ ኤሌትሪክ አምርተዋል

Wednesday, 27 December 2017 12:52

 

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያልተሳካ ጊዜን ያሳለፉት አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ኢትዮ ኤሌትሪክን ለማሰልጠን ተስማምተዋል። አሰልጣኙ በብሔራዊ ቡድን ቆይታቸው ሁለት ጨዋታዎችን ብቻ በማሸነፍ ዋልያዎቹን የተሰናበቱ አሰልጣኝ ሆነዋል።

የቀድሞው የአዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ የዛሬ አመት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በይፋ መረከባቸውን በተገለጸበት መድረክ ላይ ቡድኑን ‹‹በ2019 የአፍሪካ ዋንጫ ከምድብ ፍጻሜ አሳልፋለሁ›› ሲሉ በመናገር የብዙዎችን ትኩረት ስበው ነበር። በወቅቱ ለአፍሪካ ዋንጫው ሳያሳልፉ ምድብ ማጣሪያውን የመቀላቀል እቅድ ማሰባቸው ለትችት ዳርጓቸው እንደነበር አይዘነጋም። እሳቸው ግን በልበ ሙሉነት እምነት እንዲጣልባቸው በመጠየቅ ቃላቸውን እንደሚፈጽሙ ነበር የተናገሩት።

ይሁንና አሰልጣኙ ደካማ በሚባሉ የእግር ኳስ መድረኮች ላይ እንኳን ቡድኑን ውጤታማ ማድረግ አልቻሉም። በአፍሪካ ሊግ ውስጥ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ ያካተቱ ብሔራዊ ቡድኖች በሚሳተፉበት የቻን ውድድር ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ማሳለፍ አልቻሉም። በተለያዩ የወዳጅነት ጨዋታዎችም ላይም ይዘው የቀረቡት ሽንፈት ገጥሞታል።

በቅርቡም ኬንያ ባተናገደችውና ያለ ማጣሪያ ቡድኖች በሚሳተፉበት በምስራቅና መካከለኛው የአፍሪካ ሀገሮች የእግር ኳስ ዋንጫ (ሴካፋ) ላይም አሰልጣኝ አሸናፊ የያዙት ቡድን በምድብ ማጣሪያው ሳይሳካለት ቀርቶ በጊዜ ከውድድሩ መሰናበቱ ይታወሳል። በዘንድሮው የሴካፋ ዋንጫ የአሰልጣኝ አሸናፊ ቡድን በብሩንዲ የደረሰበት የ4ለ1 ሽንፈት ለኢትዮጵያ በመድረኩ የተሳትፎ ታሪኳ በአስከፊነቱ የተመዘገበ ሆኗል።

አሰልጣኝ አሸናፊ በአፍሪካ ዋንጫ እና በአለም ዋንጫ ማጣሪያ እንዲሁም በወዳጅነት ጨዋታዎችም ተደጋጋሚ ሽንፈት ገጥሟቸዋል። ለ2019 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በጋና 5ለ0 የተሸነፈበት ውጤት ደጋፊዎች እጅግ ካስቆጡት መካከል አንደኛው ነው። አሰልጣኙ ለሽንፈቱ ግብ ጠባቂው አቤል ማሞን ተጠያቂ ያደረጉበት ሪፖርት ከፍተኛ ትችት አሰንዝሮባቸዋል። እሳቸውም ከብሔራዊ ቡድኑ ለመለያየት ጥያቄ እንዲያቀርቡ አስገድዷቸዋል።

ከሴካፋ ዋንጫ መልስም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰልጣኝ አሸናፊ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር ለመቀጠል የሚያስችል ውጤት እንዳላስመዘገቡ በመግለጽ እንዳሰናበታቸው ተሰምቷል። ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ሁለት ጨዋታ ብቻ ያሸነፉት አሰልጣኝ አሸናፊ በጣም አስከፊ ውጤት በማስመዝገብ ከማይረሱ አሰልጣኞች መካከል አንደኛው ሆነው ይጠቀሳሉ።

ኢትዮጵያ በፊፋ ወርሃዊ የእግር ኳስ ደረጃ ሰንጠረዥ እጅግ ዝቅተኛ የሚባለውን 154ኛ ደረጃን ያገኘችው በአሰልጣኝ አሸናፊ ሀላፊነት መሆኑም በታሪክ ተመዝግቧል።

አሰልጣኝ አሸናፊ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መለያየታቸው እርግጥ ከሆነ በኋላም ወደ ኢትዮ ኤሌትሪክ ማምራታቸው ተሰምቷል። በውጤት ማጣት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ኢትዮ ኤሌትሪክ በብሔራዊ ቡድን ስኬታማ ያልሆኑትን አሰልጣኝ ተስፋ ማድረጉ ብዙዎችን አስገርሟል።

ባለፈው አመት ከሊጉ ለጥቂት ከመውረድ የተረፈው ኢትዮ ኤሌትሪክ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተደጋጋሚ ሽንፈትን በማስተናገድ ላይ ይገኛል። ክለቡ በሊጉ እስካሁን በስድስት ጨዋታዎች አምስት ነጥብ ብቻ ይዞ በስምንት ጨዋታ ተመሳሳይ አምስት ነጥብ ከያዘው ወላይታ ድቻ እኩል አንድ ደረጃ ከፍ ብሎ 15ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
73 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 237 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us