ገለቴ ቡርቃ በስፔን ድል አድርጋለች

Wednesday, 03 January 2018 17:13

አትሌት ገለቴ ቡርቃ የ2017 የውድድር አመትን በድል አጠናቃለች። በአለም ሻምፒዮና በ5 ሺህ እና 10 ሺህ ሜትር የብር ሜዳልያ ባለቤት የሆነችው ገለቴ በቀጣይ በማራቶን ርቀት የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላትም አስታውቃለች።

በቅርቡ በለንደን የአለም ሻምፒዮና ከኢትዮጵያ ቡድን ውጭ በመሆኗ ቅሬታዋን በይፋ ስትገልጽ የነበረችው አትሌት ገለቴ ቡርቃ፤ ባለፈው እሁድ በስፔን ማድሪድ በተካሔደ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫን ድል አድርጋለች። ርቀቱንም በ30፡55 ደቂቃ ያጠናቀቀች ሲሆን፤ ቀደም ሲል በ2012 በራሷ ተይዞ የነበረውን የውድድሩን ክብረወሰን ለመስበር ሁለት ሰከንዶች ብቻ ነበር የቀሯት።


‹‹በውድድሩ የራሴን ክብረወሰን ለማሻሻል አቅጄ ነበር የሮጥኩት። እቅዴን ለማሳካት የምችለውን ሁሉ ባደርግም መጨረሻ ላይ ግን ሳይሳካ ቀርቷል። ሩጫውን በማሸነፌ ግን በጣም ደስ ብሎኛል›› በማለት ከውድድሩ በኋላ አስተያየቷን ሰጥታለች።


ከ800 ሜትር ጀምሮ በትራክ ሩጫ እስከ 10 ሺህ ሜትር ድረስ በአለም አቀፍ የውድድር መድረኮች የሮጠችው ገለቴ፤ ፊቷን ወደ ማራቶን ማዞሯንም አስታውቃለች። በመጪው ወር በሚካሔደው የዱባይ ማራቶን ለመወዳደር ማሰቧንም ገልጻለች።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
84 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 247 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us