ኢትዮጵያዊያኖቹ የዱባይ ማራቶን አሸናፊዎች ዘንድሮም ይጠበቃሉ

Wednesday, 03 January 2018 17:15

የ2017 የዱባይ ማራቶን አሸናፊዎቹ ኢትጵያዊያኖች ታምራት ቶላ እና ወርቅነሽ ደገፋ ዘንድሮም ለተመሳሳይ ድል ይጠበቃሉ። በውድድሩ መድረክ የኢትዮጵያ አትሌቶች የበላይነት እንደሚታይ ይጠበቃል።

 

የአለማችን ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት የሚገኝበት የማራቶን መድረክ ዱባይ ማራቶን ከሶስት ሳምንት በኋላ ከ30 ሺህ በላይ ሰዎችን በማሳተፍ ይካሔዳል። በሩጫው መድረክ ዘንድሮም ስመ ጥር አትሌቶች እንደሚፎካከሩበት ይጠበቃል። የአምና አሸናፊዎች በወንዶች ታምራት ቶላ፤ በሴቶች ደግሞ ወርቅነሽ ደገፋ ዘንድሮም በውድድሩ መድረክ ለመሰተፍ መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።


የዱባይ ማራቶን አዘጋጆች ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ኢትዮጵያኖቹ አሸናፊዎች ታምራት ቶላ እና ወርቅነሽ ደገፋ መሳተፋቸው ውድድሩን የበለጠ ደማቅ ያደርገዋል። አሸናፊዎች የ200ሺ ዶላር ተሸላሚ የሚያደርጋቸውን የአንደኛነት ደረጃ ለማግኘት ጠንካራ ፉክክር በማሳየት መድረኩንም ተወዳጅ እንደሚያደርጉት ያደረባቸውን እምነት ገልጸዋል።


አትሌት ወርቅነሽ ደገፋ አምና ለመጀመሪያ ጊዜ በማራቶን ተሳትፋ የዱባይ ማራቶንን በ2፡22፡36 በማጠናቀቅ ማሸነፏ ይታወሳል። በመጀመሪያ የማራቶን ውድድሯ ሳትጠበቅ የ200ሺ ዶላር ያገኘችው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ዘንድሮም የመግቢያ ክፍያ ተከፍሏት የምትወዳደር ስመ ጥር አትሌት ሆናለች። ያለፈው አመት ድሏን ለመድገም መዘጋጀቷንም አትሌቷ ለአዘጋጆቹ በሰጠችው አስተያየት አስታውቃለች።


ሌላው ኢትዮጵያዊ አትሌት ታምራት ቶላም በዘንድሮው የዱባይ ማራቶን ለአሸናፊነት ከሚጠበቁ የአለማችን ስመ ጥር አትሌቶች መካከል አንደኛው ነው። አትሌቱ አምና የዱባይ ማራቶንን ያሸነፈበት ሰአት 2፡04፡11 አስረኛው የአለማችን ፈጣን የማራቶን ሰአት ነው።


ታምራት በ2016 የሪዮ ኦሊምፐክ በ10 ሺህ ሜትር የነሐስ ሜዳልያ፤ በለንደን የአለም ሻምፒዮና በማራቶን የብር ሜዳልያ ባለቤት መሆኑ ይታወሳል። የዘንድሮውን የዱባይ ማራቶን በማሸነፍ ዳግም ስሙን በድል ታሪክ ለማስመዝገብ ተዘጋጅቷል።


በ2018 የዱባይ ማራቶን ከአምና አሸናፊዎቹ አትሌቶች በተጨማሪ በርቀቱ ፈጣን ሰአት ያላቸው የኢትዮጵያና ኬንያ አትሌቶች እንደሚሳተፉ ታውቋል። ባለፉት አመታት የታየው የኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የበላይነት ታሪክ እንደሚቀጥልም ይጠበቃል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
69 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 245 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us