ፍቅሩ ተፈራ በድጋሚ ወደ ህንድ ሊግ ሊመለስ ነው

Wednesday, 03 January 2018 17:17

በደቡብ አፍሪካ ሊግ ለሱፐር ስፖርት ዩናይትድ እና ኦርላንዶ ፓይሬትስ ተጫውቶ ያሳለፈው ፍቅሩ ተፈራ በድጋሚ ወደ ህንድ ሱፐር ሊግ ሊመለስ እንደሚችል የህንድ ጋዜጦች ጽፈዋል።

 

የህንድ ሱፐር ሊግ በ2014 ሲጀመር አትሌቲኮ ካልካታ ለተባለ ክለብ በመጫወት ዋንጫ ያነሳው ፍቅሩ፤ ቼንያን ለተባለ ሌላኛው ክለብ በመፈረም ለአንድ አመት መቆየቱ ይታወሳል። በአትሌቲኮ ደ ካልካታ 12 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ በ5 ግቦች ኮከብ ግብ አግቢነት ነበር ያጠናቀቀው።


በህንድ ሱፐር ሊግ የመጀመሪያዋን ግብ ከመረብ በማሳረፍ ስሙን በሀገሪቱ የእግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ያጻፈው የቀድሞው የአዳማ ከነማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቂ፤ ለአትሌቲኮ ደ ካልካታ ዋንጫ ማንሳትም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።


ከቼንያን ጋር ከተለያየ በኋላ ወደ ደቡብ አፍሪካ አምርቶ የነበረ ሲሆን፤ አሁን ደግሞ በድጋሚ ወደ ህንድ ሱፐር ሊግ ለማምራት ድርድር ላይ መሆኑ ተዘግቧል። የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ኢስት ቤንጋል ለተባለ የእግር ኳሰ ክለብ ለመጫወት መቃረቡን ስፖርት ኪዳ የተባለ ጋዜጣ አስነብቧል። ክለቡ የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ፉክክር ላይ የሚገኝ በመሆኑ ፍቅሩን ቢያስፈርም ያለበትን የግብ አስቆጣሪ ተጨዋች ችግር ለመፍታት እንደሚያስችለው ጋዜጣው ጽፏል።


ፍቅሩ ተፈራ በበርካታ የአለማችን ሀገሮች ለሚገኙ ክለቦች በመጫወት የሚስተካከለው የኢትዮጵያ ተጫዋች የለም። ተጫዋቹ ከኢትዮጵያ ውጪ በደቡብ አፍሪካ፣ በህንድ፣ በባንግላዲሽ፣ በቬትናም፣ በፊንለንድና በቼክ ሪፐብሊክ ተዘዋውሮ ተጫውቷል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
78 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 235 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us