ደደቢትና ጌታነህ በሊጉ እየመሩ ነው

Wednesday, 17 January 2018 13:49

 

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ደደቢት የደረጃ ሰንጠረዡን፤ አጥቂው ጌታነህ ከበደ ደግሞ የኮከብ ግብ አግቢነቱን በመምራት ላይ ናቸው። ፕሪሚየር ሊጉ በተቀራራቢ ነጥብ ላይ የሚገኙ ክለቦች ከፍተኛ ፉክክር እያደረጉ ነው።

ደደቢቱ አጥቂ ጌታህ ከበደ በውጭ ሀገር ዜግነት ባላቸው ተጫዋቾች ተይዞ የነበረውን የኮከብ ግብ አግቢነት ደረጃ መረከብ ችሏል። ደደቢት እሁድ እለት በአዲስ አበባ ስታዲየም ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲን 4ለ1 ባሸነፈበት ጨዋታ ጌታነህ ያስቆጠራቸው ሁለት ግቦች ወደ ኮከብ ግብ አግቢነት እንዲመለስ አድርገውታል። እስከአሁን ያስቆጠራቸውን የግቦች ብዛት 9 ማድረስ ችሏል።

ባለፉት ሳምንታት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኮከብ ግብ አግቢነት መሪነቱን የያዙት እንደ ጃኮ አረፋትና አል ሀሰን ካሉሻን የመሳሰሉ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ተጫዋቾች እንደነበሩ ይታወሳል። አል ሀሰን ካሉሻ ጌታነህን በመከተል በ7 ግቦች ሁለተኛ ኮከብ ግብ አግቢ ሲሆን፤ ኦኪኪ አፎላቢ በ6 ግቦች ሶስተኛ ነው። ዳዋ ሁቴሳ፣ አቤል ያለውና፣ አዲስ ግደይ በእኩል 5 ግብ አራተኛ ኮከብ ግብ አግባ ሲሆኑ፤ ምንይሉ ወንድሙና ጃኮ አረፋት በ4 ግቦች ይከተላሉ።

ፕሪሚየር ሊጉን ደደቢት በ11 ጨዋታዎች በሰበሰበው 25 ነጥቦች በመምራት ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ተመሳሳይ ጨዋታ ያደረገው አዳማ ከተማ በ18 ነጥብ ሁለተኛ ነው። ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ ሁለት ተስተካካይ ጨዋታ እያለው በ17 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
78 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 233 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us