ሰላም ዘራይ የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድንን ተረክባለች

Wednesday, 17 January 2018 13:52

 

የቅዱስ ጊዮርጊስ የሴቶች እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ ሰላም ዘራይ ብሔራዊ ቡድኑን ተረክባለች። አሰልጣኟ ሉሲዎቹን ለ2018 የሴካፋ ዋጫ እና ለጋናው የአፍሪካ ዋንጫ የማሳለፍ ኃላፊነት ተሰጥቷታል።

ከሶስት ወራት የበለጠ ጊዜ የኮንትራት ስምምነት የማይሰጣቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኞች ቡድኑ ላይ በየጊዜው እየተፈራረቁ ነው። አሰልጣኝ በሀይሏ፣ መሰረት ማኒ እና ብርሀኑ ግዛው በዋናው ብሔራዊ ቡድን በየሶስት ወሩ የሚታደስ ስምምነት ተቀብለው ሲያሰለጥኑ ቆይተዋል። ከ20 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት የተቀጠሩትም አሰልጣኝ አስራት አባተ እና ሰላም ዘራይ በተመሳሳይ በየሶስት ወራቱ የሚታደስ ስምምነት ፈጽመው ማሰልጠናቸው ይታወቃል።

በወንዶቹ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቅጥር ጋር ሲነጻጸር ፈጽሞ ተቃራኒ በሆነ መንገድ ላይ መሆኑን መረዳት ይቻላል። ግልጽነት የጎደለው፣ እውቀትና ልምድን እንዲሁም ስኬትን መሰረት ያደረገ አለመሆኑን የሚናገሩ የስፖርት ቤተሰቦች አሉ። በዚህም ምክንያት የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የውድድር መድረኮች ላይ ማለፍ ተስኖታል።

ከሴቶች ብሔራዊ ቡድን የአሰልጣኞች ቅጥር ጋር በተያያዘ ተደጋጋሚ ትችት የሚደርስበት የእግር ኳስ ፌዴሬሽን በቅርቡ አሰልጣኝ ሰላም ዘራይን ለሉሲዎቹ መሪነት መምረጡ ታውቋል።

የቀድሞ ተጫዋቿ አሰልጣኝ ሰላም ከዚህ በፊት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በተጨማሪ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ምክትል አሰልጣኝ ሆና ማገልገሏ ይታወቃል። በቅርቡ ከ20 አመት በታች የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆና ቡድኑን ለ2018 የኡራጓይ የአለም ዋንጫ ለማብቃት ተቀጥራ ነበር። ይሁንና ቡድኗ አዲስ አበባ ላይ በሜዳው 2ለ2፤ በናይጄሪያ ሜዳ ያለግብ በመለያየቱ በመጀመሪያው ዙር ከማጣሪያው በጊዜ ሊሰናበት ችሏል።

አሁን ደግሞ አሰልጣኝ ሰላም ዋናውን የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለ2018 የጋናው አፍሪካ ዋንጫ እና ለሩዋንዳው የሴካፋ ዋንጫ ለማዘጋጀት ሀላፊነቱ ተሰጥቷታል። አሰልጣኟ በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ አንስታ ባታውቅም ብሔራዊ ቡድኑን ለሁለት የተለያዩ የውድድር መድረኮች ለማብቃት ከባድ ኃላፊነት ተሰጥቷታል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
64 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 238 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us