የዝውውር ወሬዎች

Wednesday, 24 January 2018 14:36

 

- የአመቱ የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋች መሀመድ ሳላህ ለበክረምቱ የዝውውር መስኮት ወደ ስፔኑ ሪያል ማድሪድ ሊያቀና እንደሚችል ተገምቷል። የ25 አመቱ ግብጻዊ አጥቂ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ያሳየው ብቃት በብዙ ክለቦች ተፈላጊ እንዲሆን አድርጎታል። ተጫዋቹን ለማስፈረም ግን ዳጎስ ያለ የገንዘብ መጠን ያቀረበው ማድሪድ የተሻለ እድል እንዳለው የግብጽ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ማስታወቃቸውን ሊቨርፑል ኤኮ ዘግቧል።

- አርሴናል ለማቸስተር ዩናይትድ በሸጠው አሌክሲስ ሳንቼዝ ምትክ ተጫዋች ለማስፈረም እየጣረ ነው። የቦርሲያ ዶርትሙንዱ አጥቂ ፒየር ኤሪክ አቡሜያንግ ደግሞ የአርሴን ቬንገርን ልዩ ትኩረት ያገኘ ተጫዋች ነው። የጋቦኑ አጥቂ በቦርሲያ ዶርትሙንድ ስኬታማ ጊዜን አሳልፏል፡ የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋች ያደረገውን ብቃትም አሳይቷል። ተጫዋቹ ለመድፈኞቹ ክለብ ለመጫወት ከፍተኛ ፍላጎት ስላለው ዝውውሩ እንደሚሳካ ተገምቷል።
- ቦርሲያ ዶርትንድ ከአቡሜያንግ ዝውወር ጋር በተያያዘ አርሴናል ፈረንሳዊውን አጥቂ ኦሊቨር ዥሩን እንዲሰጠው ጥያቄ አቅርቧል። የ31 አመቱ ዡሩ በአርሴናል ቋሚ ተሰላፊነት እያጣ በመሆኑ አርሰን ቬንገር ሊለቁት ይችላሉ ተብሏል።
- የኒውካስል ዩይትድ አሰልጣኝ ራፋኤል ቤኒቴዝ በክለቡ ለመቆየት የሚያስችላቸውን ውል ማራዘሚያ ስምምነት ቀርቦላቸዋል። ይሁንና የቀድሞው የሊቨርፑል አሰልጣኝ በክለቡ መቆየት እንደማይፈልጉ ነው የተዘገበው።
- ቼልሲ የስቶክ ሲቲውን አጥቂ ፒተር ክራውችን ለማስፈረም የሚያደርገውን ድርድር አጠናክሮ ቀጥሏል። የክለቡ ሀላፊ ፖል ላምበርት ግን የ36 አመቱ ተጫዋች ለዝውውር እንደማያቀርቡት ነው ያስታወቁት።
የቼልሲው አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ የ31 አመቱን አጥቂ ኤዲን ዜኮን ከሮማ ለማስፈረም ይፈልጋሉ። አሰልጣኙ ከዚያው ከጣሊያኑ ክለብ ከዜኮ በተጨማሪ የ23 አመቱን ተጫዋች ኤመርሰን ፓለምሪን ለማዛወር መቃረባቸው ተዘግቧል።¾

 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
71 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 269 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us