ቀነኒሳ በቀለ በለንደን ማራቶን ለሶስተኛ ጊዜ ይወዳደራል

Wednesday, 24 January 2018 14:42


 

የአለምና የኦሎምፒክ አሸናፊው ቀነኒሳ በቀለ በ2018 የለንደን ቨርጂን ማራቶን ለአዲስ ታሪክ ለማስመዝገብ ይሮጣል። በውድድሩ ከአለማችን ምርጥ ሯጮች ከኬንያዊው ኢውድ ኪፕቾጌ እና እንግሊዛዊው ሞ ፋራህ ጋር የሚያደርጉት ፉክክር ከወዲሁ አጓጊ ሆኗል።


በመም (ትራክ) ላይ ሩጫዎች የላቀ የአሸናፊነት ታሪክ በማስመዝገብ ከጥቂት ድንቅ የአለማችን አትሌቶች መካከል አንዱ የሆነው ኢትዮጵያዊው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በማራቶን ሩጫም ተመሳሳይ ድል የማስመዝብ ፍላጎት አለው። በዘንድሮው የለንደን ማራቶን ከአሸናፊነትም በላይ የርቀቱን የአለም ክብረወሰን ለማስመዝገብም ነው የሚወዳደረው።


የለንደን ማራቶን ከሁለት ወር በኋላ የሚካሔድ ሲሆን፤ በሁለቱም ጾታ የአለማችን ፈጣን ሰአት ባለቤቶች ይካፈሉበታል። በወንዶቹ ከቀነኒሳ በቀለ በተጨማሪ ወደ ጎዳና ሩጫ ያመራው ሞ ፋራህና ከርቀቱ የወቅቱ ምርጥ ሯጭ ኢውድ ኪፕቾጌ ጋር በውድድሩ ላይ እንደሚሳተፉ ታውቋል።


የ34 አመቱ ቀነኒሳ ባለፉት ሁለት አመታት በለንደን ማራቶን የውድድር መድረኮች ላይ የተሳተፈ ሲሆን፤ በ2016 ላይ ርቀቱን በ2፡06፡03 በማጠናቀቅ ሶስተኛ ደረጃን ነበር ያገኘው። ባለፈው አመት ደግሞ ዳንኤል ዋንጅሩን ተከትሎ በመግባት ርቀቱን 2፡05፡57 ማጠናቀቁ ይታወሳል። በዘንድሮው አመት ደግሞ ካለፉት ጊዜያት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚሮጥ ነው ያስታወቀው።


‹‹በለንደን ማራቶን ለሶስተኛ ጊዜ ለመሳተፍ በመቻሌ በጣም አስደስቶኛል። ውድድሩን ማሸነፍና ካለፈው አመት በተሻለ ሁኔታ ለማጠናቀቅ እፈልጋለሁ። በእርግጥ ለንደን ማራቶን ላይ የአለም ምርጥ ሯጮች ስለሚሳተፉ ቀላል እንደማይሆንልኝ አውቃለሁ። እኔም ለውድድሩ ከፍተኛ ዝግጅት እያደረኩ ነው። ከጠንካራ ራጮቹ ከሞ ፋራህ እና ኢውድ ኪፕቾጌ ጋር የምወዳደር በመሆኔም በጣም ደስ ብሎኛል›› ሲል ቀነኒሳ ለውድድሩ አዘጋጆች አስተያየቱን ሰጥቷል።


ቀነኒሳ በማራቶን በርሊን ላይ ያስመዘገበው 2፡03፡03 ሰአት የርቀቱ የአለማችን የዓመቱ ፈጣን ሰአት ነው። ይህንን ሰአት በማሻል የአለም ክብረወሰንን የመስበር ፍላጎት እንዳለው በተደጋጋሚ ሲናገር ተደምጧል። ይህንንም በለንደን ማራቶን ሊያሳካው እንደሚችልም ይጠበቃል።


ከቀነኒሳ ጋር አብረው ከሚወዳደሩት መካከልም ኬንያዊው ኢውድ ኪፕቾጌ ከፍተኛ የአሸናነት ግምት ያለው ሯጭ ነው። አትሌቱ በቅርቡ ይፋዊ እውቅና ባይሰጠውም በማራቶን የአለም ክብረወሰንን የሰበረ ሰአት ማስመዝገቡ ይታወሳል።


ሌላው የሚጠበቀው አትሌት ከትራክ ሩጫዎች ራሱን ያሰናበተው ሞ ፋራህ በሀገሩና በደጋፊዎቹ ፊት የሚያደርገውን ሩጫ በበላይነት ለማጠናቀቅ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
71 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 246 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us