ዩዚየን ቦልት በደቡብ አፍሪካ የእግር ኳስ ልምምድ እያደረገ ነው

Wednesday, 31 January 2018 13:21

 

በአጭር ርቀት ሩጫ የአለምና የኦሊምፒክ አሸናፊው ዩዚየን ቦልት በደቡብ አፍሪካው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ የእግር ኳስ ክለብ ውስጥ ልምምድ በማድረግ ላይ ነው። የጀርመኑ ቦርሱያ ዶርትሞንድም ለጃማይካዊው የአጭር ርቀት ንጉስ ግብዣ አቅርቦለታል።


ከአንድ አመት በፊት የትራክ ሩጫን የተሰናበተው ጃማይካዊው ዩዚየን ቦልት ወደ እግር ኳስ ተጫዋችነት የመሻገር ህልሙን እውን ለማድረግ በእርግጥም የወሰነ ይመስላል። መደበኛ የእግር ኳስ ልምምዶችን እየሰራ ነው። በተለያዩ ክለቦች ገብዣ የቀረበለት ሲሆን፤ የስፖንሰሩ ፑማ ድጋፉ በሚያገኘው በደቡብ አፍሪካው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ክለብ የመጀመሪያውን ይፋዊ ልምምድ መስራትን መርጧል።


የክለቡ አሰልጣኝ ፒሶ ሞሲማኒ ቦልት በክለባቸው ልምምድ ለመስራት መፍቀዱ እንዳስደሰታቸው ገልጸው አትሌቱን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው አስታውቀዋል። “ተፈጥሯዊ ተክለ ሰውነቱና ፍጥነቱ የሚሰጠውን ጠቀሜታ በማሰብ እርሱ በፈለገው ቦታ ልናጫውተው እንፈልጋለን” ብለዋል።


ቦልት በደቡብ አፍሪካው ክለብ የሚኖረውን የአጭር ጊዜ ቆይታ ካጠናቀቀ በኋላ ቀጣይ ውሳኔው ምን እንደሆነ አልታወቀም። የቦርሲያ ዶርትሞንድ እግር ኳስ ክለብ ከቡድኑ ጋር ልምምድ እንዲያደርግ ያቀረበለትን ግብዣ ተቀብሎ ወደ ጀርመን ስለማቅናቱም የታወቀ ነገር የለም።


የ28 አመቱ ቦልት ለእንግሊዙ ማንቸስተር ዩናይትድ ክለብ የመጫወት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው በተደጋጋሚ መናገሩ ይታወቃል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
60 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 250 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us