የባህር ዳር ከነማ እና ሽረ እንደስላሴ ጨዋታ ለአራተኛ ጊዜ ተራዘመ

Wednesday, 31 January 2018 13:24

 

በይርጋ አበበ

 

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ (ሱፐር ሊግ) ተወዳዳሪ የሆኑት የአማራ ክልሉ ባህር ዳር ከነማ እና የትግራዩ ሽረ እንደስላሴ እግር ኳስ ክለቦች ጨዋታ ለአራተኛ ጊዜ ትናንት ተራዘመ።
የባህር ዳር ከነማ እና ሽረ እንደስላሴ ጨዋታ ባሳለፍነው ቅዳሜ በሰበታ ስታየም ይካሄዳል ተብሎ የነበረ ሲሆን እንደገና ወደ ለገጣፎ ከተማ እንዲዛወር ተደርጎ ጨዋታው በዕለቱ ሳይካሄድ ቀረ። ክለባቸውን ለመደገፍ ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ የመጡ የባህር ዳር ከነማ ደጋፊዎች ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለጹት ጨዋታው እንደማይካሄድ ተነግሯቸው ወደ ከተማቸው እየተጓዙ ሳለ ደጀን ከተማ ሲደርሱ ጨዋታው በኦሜድላ ሜዳ እንደሚካሄድ ሲነገራቸው ተመልሰው አዲስ አበባ ገብተው አደሩ።


ሆኖም ጨዋታው ሊጀመር የሁለቱም ቡድኖች ተጫዋቾች እያሟሟቁ እና ዳኞችም የጨዋታውን ተሰላፊዎች ከመዘገቡ በኋላ ጨዋታው እንደማይካሄድ እንደተነገራቸው ከደጋፊ ማህበሩ የሚዲያ አባል የሆነው ቃልኪዳን ጠና ተናግሯል።
ጨዋታው በሽረ ከተማ መካሄድ የነበረበት ቢሆንም በወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት በገለልተኛ ሜዳ እንዲካሄድ በፌዴሬሽኑ መወሰኑ ይታወሳል። ለአራተኛ ጊዜ የተራዘመው ጨዋታ መቼ እንደሚካሄድ ለማጣራት ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ኃላፊዎች ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
112 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 269 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us