ጥሩነሽ ዲባባ ለለንደን ማራቶን እየተዘጋጀች ነው

Wednesday, 31 January 2018 13:26

 

ጥሩነሽ ዲባባ ለዘንድሮው የ2108 የለንደን ማራቶን ዝግጅት እያደረገች ነው። በውድድሩ ከአምናው የተሸለ ውጤት ለማስመዝገብ እንደምትሮጥም አስታውቃለች።
በትራክ ላይ ሩጫ ስኬታማ ጊዜያትን ያሳለፈችው ጥሩነሽ ዲባባ ሙሉ ለሙሉ ትኩረቷን ወደ ማራቶን አድርለች። ከሁለት ወር በኋላ ለሚካሔደው የለንደን ማራቶንም ጠንካራ ዝግጅት እያደረገች ነው። በውድድሩ መድረክ አምና ያስመዘገበችውን የሁለተኛነት ውጤት አሻሽላ አንደኛ ለመግባት ማቀዷን አስታውቃለች።


ጥሩነሽ ባለፈው አመት በለንደን ማራቶን ሩጫ ላይ በድንገት የገጠማትን ህመም ተቋቁማ ሁለተኛ ደረጃ መግባቷ ይታወሳል። ርቀቱን ያጠናቀቀችት 2፡17፡56 ሰአት የኢትዮጵያ አዲስ የማራቶን ክብረወሰን ሆኖ ተመዝግቧል። ከአለም ደግሞ ሶስተኛው ፈጣኑ የማራቶን ሰአት ነው። ዘንድሮ ይህንን ሰአት ለማሻሻል የሚያስችላትን ዝግጅት በማድረግ እንደምትወዳደር ነው ለአዘጋጆቹ ያስታወቀችው።


ከጥሩነሽ ዲባባ በተጨማሪ በለንደን ማራቶን ጠንካራ አትሌቶች እንደሚሳተፉ ታውቋል። ትዕግስት ቱፋና ማሬ ዲባባን የመሳሰሉ የኢትዮጵያ አትሌቶች ይሮጣሉ።
በተመሳሳይ መድረክ በወንዶቹ ቀነኒሳ በቀለ የሚሳተፍ ሲሆን፤ ጉዬ አዶላም ሌላው የሚጠበቅ የኢትዮጵያ አትሌት ነው።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
61 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 238 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us