በዱባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ አግኝተዋል

Wednesday, 31 January 2018 13:29


 

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዘንድሮው የ2108 የዱባይ ማራቶን ውድድር ለሽልማት ከተዘጋጀው ገንዘብ አብዛኘውን ጠራርገው የወሰዱበትን ውጤት አስመዝግበዋል። በሁለቱም ጾታ እስከ አስረኛ ያለውን ደረጃ ውስጥ ለገቡ አትሌቶች ከተዘጋጀው የገንዘብ ሽልማት ውስጥም ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ አግኝተዋል።


ባለፈው አርብ ለ19ኛ ጊዜ በተካሔደው የዱባይ ማራቶን በሴቶች ሮዛ ደረጀ፤ በወንዶች ሞስነት ገረመው አሸንፈዋል። ሁለቱ አትሌቶች እያንዳንዳቸው ለአሸናፊዎች የተዘጋጀውን የ200,000 የአሜሪካን ዶላርም ሽልማት ወስደዋል። ሁለተኛ ደረጃን ያገኙት ፈይሴ ታደሰ በሴቶች እና ልዑል ገብረስላሴ በወንዶቹ የ80,000 ዶላር፤ እንዲሁም ሶስተኛ ደረጃ የገቡት የብርጓል መለሰ በሴቶች እና ታምራት ቶላ በወንዶች የ40,000 ዶላር ተሸላሚ ሆነዋል።


በውድድሩ እስከ 10ኛ ደረጃን ይዘው ላጠናቀቁ አትሌቶች እንደ የደረጃቸው የገንዘብ ሸልማት ይሰጣል። 10ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ አትሌቶች የ10,000 ዶላር ሽልማት ያገኛሉ። በሁለቱም ጾታ የበላይነት የነበራቸው ኢትዮጵያ አትሌቶች ሁሉንም ለማለት በሚያስደፍር ሁኔታ ገንዘቡን ጠራርገው ወስደዋል።


በወንዶች እስከ አስረኛ ያለው ደረጃ በተከታታይ በኢትዮጵያ አትሌቶች የተያዘ ሲሆን፤ በአጠቃላይ አስሩ አትሌቶች 408,000 ዶላር ወስደዋል። በሴቶች ለባህሬን ከምትሮጠው አትሌት ከተያዘውና 11,000 ዶላር ከሚያሸልመው ከ8ኛ ደረጃ በስተቀር የኢትዮጵያ አትሌቶች እስከ አስረኛ ገብተዋል። ዘጠኙ አትሌች 397,000 ዶላር ለመውሰድ ችለዋል። ይህም በሁለቱም ጾታ 19 የኢትዮጵያ አትሌቶች ተሸላሚ የነበሩ ሲሆን፤ 816,000 ዶላር ወይም በወቅቱ የኢትዮጵያ ምንዛሪ ከ21 ሚሊዮን 32 ሺህ ብር የሚጠጋ ሽልማት ወስደዋል። ይህም በውድድሩ የኢትዮጵያውያን የተሳትፎ ታሪክ ከፍተኛ ገንዘብ የወሰዱበት ሆኖ እንዲጠቀስ አድርጎታል።


ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት በመሸለም የአለማችን ሀብታሙ የማራቶን መድረክ በሆነው የዱባይ ማራቶን፤ ዘንድሮ በሁለቱም ጾታ የአምናው የቦታው ክብረወሰን ተሻሽሏል። ባለፈው አመት በወንዶች በታምራት ቶላ የተመዘገበው የቦታው ክብረወሰን ዘንድሮ ሞስነት ገረመው ርቀቱን 2፡04፡00 በመግባት በ10 ሰከንዶች አሻሽሎታል። በማራቶን ሰባተኛው የአለም ፈጣን ሰአት ባለቤትም አድርጎታል። የአለም የማራቶን ክብረወሰን በኬንያዊው ዴኒስ ኪሜቶ 2፡57፡00 የተያዘ ሲሆን፤ ቀነነኒሳ በቀለ 2፡03፡03 ሀለተኛው ፈጣን ሰአጥ ነው።


በዱባይ ማራቶን በውድድሩ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ለሚይዙ አትሌቶች የሚሰጠው የሽልማት መጠን ሰፊ ልዩነት መኖሩ መድረኩን ጠንካራ ፉክክር የሚካሔድበትና ፈጣን ሰአትም የሚመዘገብበት አድርጎታል። በወንዶቹ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰባት አትሌቶች ከ2፡05 በታች የገቡበት መድረክ ሆኗል።


በሴቶችም መካከል በተካሔደው ፉክክር ስድስት የኢትዮጵያ አትሌቶች ርቀቱን 2፡20 በታች የገቡበት ሆኖ ተመዝግቧል። ሮዛ ደረጀ በዘንድሮው የዱባይ ማራቶን ርቀቱን 2፡19፡17 በማጠናቀቅ የቦታውን ክብረወሰን ማሻሻል ችላለች።

Last modified on Wednesday, 31 January 2018 13:37
ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
78 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 241 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us