ወልዲያ ከተማ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ተመልሷል

Wednesday, 14 February 2018 12:11

 

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ የሆነው የወልዲያ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ በሚል ምክንያት የተበተነው ቡድኑ እንደገና መሰባሰቡ ተሰምቷል። በቀጣዩ አርብ እለትም ሶደ ላይ ከወላይታ ዲቻ ጋር ይጫወታል።


የወልዲያ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ባለፉት ሶስት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ሳይሳተፍ ቀርቷል። ቡድኑን እንደገና ለማሰባሰብ የተደረገው ጥረት በከፊል ተሳክቶ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መመለሱ ታውቋል። ባለፈው እሁድ ከወላይታ ዲቻ ጋር ሊያደርግ የነበረውን ጨዋታም በተስተካካይ የጨዋታ መርሀ ግብር የፊታችን አርብ ያከናውናል።


የወልዲያ መመመለስ ለአካባቢው ወጣቶችና ለክለቡ ደጋፊዎች ደስታን የፈጠረ መልካም ዜና ሆኗል። ይሁንና በክለቡ የሚገኙ ስመጥርና ተስፈኛ ተጨዋቾች በቡድኑ ውስጥ የመቆየታቸው ነገር አጠራጣሪ ሆኗል። ተጫዋቾቹ በተረጋጋ መንፈስ ደህንነት ተሰምቷቸው መጫወት የማይችሉበት ሁኔታ የሚከሰት ከሆነና ክለቡም በችግር ጊዜ ቡድኑን ከመበተን ይልቅ የተሻሉ አማራጮችን መፍጠር የማይችል ከሆነ የመውጫ በሩን መመልከታቸው አይቀርም።
ወልዲያ ከነማ በፕሪሚየር ሊጉ የአርቡን ጨምሮ አራት ቀሪ ተስተካካይ ጨዋታዎች እያሉት በ11 ጨዋታዎች 11 ነጥቦችን አሉት። በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ መጨረሻ ከሚገኘው ኢትዮ ኤሌትሪክ አንድ ደረጃ ከፍ ብሎ 15ኛ ደረጃን ይዟል። አርብ ከወላይታ ዲቻ ጋር ካደረ በኋላ ቀሪ የተስተካካይ ጨዋታዎቹ ከመከላከያ፣ ከኢትዮ ኤሌትሪክ እና ከደደቢት ጋር ያከናውናል።

Last modified on Wednesday, 14 February 2018 12:28
ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
70 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 607 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us