“ቅድሚያ ለሴቶች ሩጫ” ለ15ኛ ጊዜ ይካሔዳል

Wednesday, 14 February 2018 12:13

 

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በየአመቱ የሚያዘጋጀው ‹‹ቅድሚያ ለሴቶች›› የ5ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ ሩጫ መጋቢት 2 ቀን ለ15ኛ ጊዜ ይካሔዳል። የሩጫው ምዝገባ መጀመሩንም አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
የዘንድሮው የቅድሚያ ለሴቶች ሩጫ ‹‹ከጥቃት ነጻ ህይወት መብቴ ነው›› በሚል መሪ ቃል የሚካሔድ ሲሆን፤ ወጣትና ስመ ጥር ሴት አትሌቶችን ጨምሮ ከ12ሺ በላይ ተሳታፊዎች ይካፈሉበታል። በተለያዩ ሙያዎች የተሰማሩና በተምሳሌትነት የሚጠቀሱ 30 ሴቶችም በሩጫ መድረኩ እንደሚሳተፉ ታውቋል።


ሩጫው ለ15ኛ ጊዜ መካሔዱን አስመልክቶም ባለፈው ሐመስ በአትሌት መሰረት ደፋር የቀድሞ ትምህርት ቤት በፊትአውራሪ ሀብተጊዮርጊስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ልዩ መርሀግብር ተካሒዶ ነበር። በዝግጅቱም ላይ እንደ ሀይሌ ገብረስላሴ፣ ጌጤ ዋሚና መሰረት ደፋር ያሉ የአለምና የኦሊምፒክ አሸናፊ አትሌቶች ተገኝተዋል። ከሴት ልጆች ከጥቃት ነጻ ህይወት ጋር በተያያዘ አነቃቂ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል። ከተማሪዎች ጋርም በመጫወት ሴቶች በነጻነት መማርና ችሎታቸውን መጠቀም እንደሚችሉ መልዕክቶን አስተላልፈዋል።


የቅድሚያ ለሴቶች አመታዊ የሩጫ መድረክን ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከተባበሩት መንግስታትና ከሌሎች አጋሮች ጋር በመሆን የሚያዘጋጀው ሲሆን፤ የሴቶች ጥቃትን ለማስቆም የሚያስችሉ መልዕክቶች የሚተላለፍበት ነው። በሩጫው ላይ ለመሳተፍ

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
75 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 419 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us