የአሰልጣኝ ንጉሴ ቅጣት አነጋጋሪ ሆኗል

Wednesday, 14 February 2018 12:19

 

በደደቢቱ ዋና አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ ላይ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተላለፈው ቅጣት በስፖርት ቡተሰቡ ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል። አሰልጣኙ ለሶስት ወር ቡድኑን ሜዳ ውስጥ እንዳይመራ የተላፈው ቅጣት በረጅምነቱ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።


በኢትዮጵያ ፕሩሚየር ሊግ ደደቢት በጅማ ከነማ መሸነፉን ተከትሎ አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ የሰጡት አስተያየት አስገራሚና ያልተጠበቀ የተባለ ቅጣት እንዲተላለፍበት አድርጓል። አሰልጣኙ ቡድናቸው ሽንፈት ከደረሰበት በኋላ በሰጡት አስተያየት ያልተገባ የዳኝነት በደል እንደተፈጸመበት ተናግረዋል። ደደቢትን ለማጥፋት የተጠነሰሰ ሴራ መኖሩን በግልጽ የሚያሳይ ነው የሚል አስተያየትም ሰጥተው ነበር።
አሰልጣኙ የሰጡት አስተያየት በወቅቱ በብዙዎች ዘንድ ለትችት አጋልጧቸው ነበር። ክለቡ ግን አልደገፋቸውም። ይልቁንም በይፋ በሰጠው መግለጫ አሰልጣኝ ንጉሴ የተናገሩት አስተያየት የግል ስሜታቸው እንደሆነና ክለቡን እንደማይወክልም ነው ያረጋገጠው።


የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም አሰልጣኙ በመገናኛ ብዙሀን የሰጡት አስተያየት ጤናማ ያልሆነና የእር ኳስን የመቻቻል መርህ የጣሰ መሆኑን በመረዳት የጨዋታ እገዳና የገንዘብ ቅጣት አስተላልፎባቸዋል። አሰልጣኙ ለሶስት ወሮች ቡድናቸውን እየመሩ ሜዳ እንይገቡ የሚደርግና የ20.000 ብር (ሀያ ሺ ብር) የገንዘብ ቅጣት አስተላልፎባቸዋል።


በአሰልጣኙ ላይ የተጣለው የሶስት ወር ጨዋታ ያለመምራት እገዳ እጅግ የበዛና የገንዘብ ቅጣቱ ያነሰ መሆኑን የሚናገሩ አስተያየት ሰጪዎች ገንዘቡን ከፍ ቢል የተሻለ እንደሆነ ይናገራሉ። በአንጻሩ ደግሞ አሰልጣኙ የሰጡት አስተያየት አደገኛነትን በመግለጽ፤ ቅጣቱ ተገቢና ለሌሎችም አስተማሪ መሆኑን የሚናገሩም አሉ።


በቅጣቱ ዙሪያ የደደቢት እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኙን ወግኖ በመቆም ይግባኝ ይጠይቃል ተብሎ ይጠበቅ ነበር። ይሁንና ክለቡ ባልፈጸመው ቅጣት ይግባኝ አይጠይቅም ሲል የፌዴሬሽኑን ውሳኔ በጸጋ መቀበሉን ነው ያታወቀው። በዚህም የተነሳ ደደቢት በቀጣይ አሰልጣኙ ጋር የሚኖረው ቆይታ አጠያያቂ ሆኗል።


በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሰልጣኝ ንጉሴ ላይ የተላለፈው አይነት ቅጣት እስካሁን ተግባራዊ ሆኖ አለማወቁ ትኩረት ስቧል። በተለይም ደግሞ አሰልጣኞች በሚሰጡት አስተያየቶች ተመሳሳይ ቅጣት በቅርብ አመታት ታይቶ አያውቅም።


አሰልጣኞች በመገናኛ ብዙሀን አስተያየታቸውን የመስጠት ልማድን የጀመሩት በቅርብ አመታት በመሆኑና የሚያስቀጣና የማያስቀጣ አስተያየቶች ላይ በቂ እውቀት አላቸው ተብሎ አይታሰብም። አሰልጣኞቹ በዚህ ዙሪያ ራሳቸውን በእውቀትና በስነ ምግባር ማነጽ ይጠበቅባቸዋል።


የገንዘብ ቅጣቶችን በመጣል ተደጋጋሚ ውሳኔዎችን በማስተላለፍ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም አሰልጣኞች በመገናኛ ብዙሀን በሚሰጧቸው አስተያየቶች ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው መስራት እንደሚገባው ብዙዎች ይስማማሉ።


ደደቢት ከአሰልጣኙ እገዳ በኋላ ሰኞ እለት ከመከላከያ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 4ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። ፕሪሚየር ሊጉንም በ13 ጨዋታዎች በ28 ነጥብ እየመራ ይገኛል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
75 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 385 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us