ወላይታ ዲቻ በዛንዚባር ነጥብ ተጋርቶ ተመልሷል

Wednesday, 14 February 2018 12:21

 

- ክለቡ ለተጫዋቾቹ የገንዘብ ሽልማት ሰጥቷል

 

የወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ክለብ ወደ ዛንዚባር በመጓዝ ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረገውን የኢንተርናሽናል ጨዋታ በአቻ ውጤት ማጠናቀቁ ክለቡንና ደጋፊዎቹን አስደስቷል። ክለቡም ተጫዋቾቹ ላስመዘገቡት ውጤት ቃል የገባውን የገንዘብ ሽልማት አበርክቷል።

 

ያለፈው አመት የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫን በማሸነፉ በዘንድሮው የካፍ ኮንፌዴሬሽንን ዋንጫ ላይ ተሳታፊ የሆነው ወላይታ ዲቻ፤ የመጀመሪያ ኢንተርናሽናል ጨዋታውን ከዛንዚባሩ ዚማማቶ ክለብ ጋር አድጓል። ቡድኑ በኮንፌዴሬሽን የቅድመ ማጣሪያ ከሜዳው ውጪ ያደረገውን ጨዋታ በአቻ ውጤት ነው ያጠናቀቀው። ክለቡ ከሜዳው ውጪ ግብ ማስቆጠሩ በሜዳው የሚያደርገውን የመልስ ጨዋታ ያለ ከፍተኛ ጫና እንዲጫወት ያደርገዋል።
ወላይታ ዲቻ በሀገር ውስጥ በውጤት መዋዠቅ ቢቆይም፤ በታሪኩ የመጀመሪያ በሆነው የኢንተርናሸናል ጨዋታው ከሜዳው ውጪ ግብ በማስቆጠር ነጥብ በመጋራት ቀጣይ ጉዞውን ተስፋ ሰጪ አድርጓል። የመልስ ጨዋታውን እንሚያሸንፍም ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶታል።


የዚማማቶና ወላይታ ዲቻ ጨዋታ የመጀመሪያ አጋማሽ ያለ ግብ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ ዲቻዎች የተሻለ የኳስ ቁጥጥር፤ ዚማማቶ ደግሞ በግብ ሙከራዎች የበላይነት እንደነበራቸው ዘገባዎች አመልክተዋል።


በሁለተኛው አጋማሽ ላይም የኢትዮጵያው ክለብ ኳስን በመቆጣጠር ተጋጣሚው ላይ የነበረውን ብልጫ መድገም ችሏል። ግብን በማስቆጠር ግን ባለሜዳው ክለብ ነበር የቀደመው። ሀኪም ካሚስ በተባለ ተጫዋች ከዲቻው ግብ ጠባቂ በቅርበት ተገናኝቶ ኳስን ከመረብ አሳርፏል።


ለዲቻ ጠቃሚ የሆነችውን ግብ ደግሞ የቶጎው አጥቂ ጃኮ አራፋት ነው ያስቆጠረው። አማካይ ተጫዋቹ ዳግም በቀለ ወደ ግብ የመታትን ኳስ ግብ ጠባቂው በመመለስ ቢያድናትም ግቡ አካባቢ የነበረው ጃኮ አራፋት ኳሷን ወደ ግብነት መቀየር ችሏል።


የሁለቱ ክለቦች የመልስ ጨዋታ ከሁለት ሳምንት በኋላ የሚያደርግ ሲሆን፤ ወላይታ ዲቻ የሐዋሳ ስታዲየምን መርጧል። በመልሱ ጨዋታም ከበርካታ ደጋፊዎቹ የድጋፍ ዜማ በመታጀብ ድል እንደሚያደርግ ተገምቷል።
ወላይታ ዲቻ በደርሶ መልሱ ጨዋታ ተጋጣሚውን ማሸነፍ ከቻለ በዋናው ማጣሪያ በመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ከግብጹ ዛማሌክ ጋር የሚገናኝ ይሆናል። በካፍ ቻምፒየንስ ሊግና ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የአሸናፊነት ታሪክም ያለው ዛማሌክ፤ በዚህ ሳምንት በግብጽ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።


በዘንድሮው የኢትየጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወጥ አቋም ማሳየትና ውጤት ማስመዝገብ የተቸገረው ዲቻ የረጅም ጊዜ የቡድኑን አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪንና ምክትሉን አሰናብቶ አሰልጣኝ ዘነበን በጊዜያዊነት መሾሙ ይታወሳል። በፕሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥም ቀሪ ጨዋታዎች እያሉት ባደረጋቸው 13 ጨዋታዎች 16 ነጥብ ይዞ 9ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።


ክለቡ ከዛንዚባሩ ክለብ ጋር አቻ ውጤት በማስመዝገቡ ለእያንዳንዱ ተጫዋች ቃል የገባውን የ10ሺ ብር ሽልማት መስጠቱ ታውቋል። ጨዋታውን በያሸንፉ ኖሮ 20ሺብር ሽልማት ይሰጣቸው ነበር።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
75 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 467 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us