የጊኒን ቡድን ለማሰልጠን ከ80 በላይ አመልካቾች ቀርበዋል

Wednesday, 21 February 2018 12:13


የምዕራብ አፍሪካዊቷን ሀገር ጊኒን ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ለማሰልጠን ከመላው አለም ከ80 በላይ አሰልጣኞች መቅረባቸው ተሰምቷል። የጊኒ ቡድን በርካታ አሰልጣኞች ለውድድር የቀረቡበት የአለማችን አንደኛው ብሔራዊ ቡድን መሆኑ ትኩረት ስቧል።

 

የጊኒ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሰሞኑን እንዳስታወቀው የሀገሪቱን ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ለማሰልጠን ከተለያዩ የአለማችን ሀገሮች ከ80 በላይ አመልካቾች ቀርበዋል። አብዛኛዎቹ አሰልጣኞችም ስመ ጥርና ልምድ ላቸው መሆናቸው ምርጫውን ፈታኝ አድርጎብኛል ብሏል።


ጊኒ በቅርቡ ሞሮኮ ላይ በተካሔደው የቻን ውድድር ውጤታማ አለመሆኗን ተከትሎ አሰልጣኙ ላፔ ባንራን ማሰናበቷ ይታወሳል። የአሰልጣኙ ስንብትን ተከትሎም አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ያወጣችው ማስታወቂያ በርካቶች ማመልከታቸው ያልጠጠበቀ ሆኗል።


‹‹ከ80 በላይ አሰልጣኞች ማመልከተቻው ለዕኘ የልጠበቅነው ሆኖብናል። ብወቹም በከፍተኛ ደረጃ የአሰልጣኝነተ ልምድም ሆነ ውጤት ያላቸው ናቸው። ከመካከላቸው አንደኛውን መምረጥ በጣም ፈታኝ ስራ መሆኑ አይቀርም›› በማለት የእግር ኳስ ፌደሬሽኑ ባወጣው መግለጫ ላይ አስታውቋል። በቀጣይም አመልካቾቹን የመጀመሪያ ዙር ማጣራት በመለየት በቃል ወደሚደረገው ድርድር እናመራለን ብሏል።


የጊኒ ብሔራዊ ቡድንን ለማሰልጠን የሚቀጠረው አዲስ አሰልጣኝ ዋነኛ ሀላፊነት ቡድኑን ለ2019 የአፍሪካ ዋንጫ ማብቃት መሆኑን የሀገሪቱ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ብሔራዊ በቡድኑ ለአፍሪካ ዋንጫው ከሴንትራል አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ከአይቮሪኮስትና ከርዋንዳ ጋር መመደቡ ይታወቃል።


በካሜሮን በሚካሔደው የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ ከምድባቸው አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ይዘው የምድብ ማጣሪያውን የሚያጠናቅቁ ቡድኖች ለውድድሩ የሚያልፉ ይሆናል።
ኢትዮጵያ ባዘጋጀችው በ1976 የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ሁለተኛ ሆና ያጠናቀቀችበት ታሪኳ ብቻ በውድድሩ ታሪክ በስኬት ይጠቀሳል። በፊፋ የአለም ዋንጫ ውድድሮች ላይም ተሳትፋ የማታውቀው ጊኒ በቀጣይ ብሔራዊ ቡድኗ በአፍሪካም ሆነ በፊፋ የአለምዋንጫ መድረኮች ጠንካራ ተፎካካሪ ለማድረግ እየሰራች መሆኗን አስታውቃለች።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
98 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 774 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us