አሰልጣኝ አሸናፊ የመጀመሪያ ድላቸውን አስመዘገቡ

Wednesday, 21 February 2018 12:15


በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ያልተሳካ ጊዜ ያሳለፉት አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ኢትዮ ኤሌትሪክን ከተረከቡ በኋላ ውጤት ርቋቸው ቆይቶ ነበር። ባለፈው ሰኞ እለት ግን ለመጀመሪያ ጊዜ ሶስት ነጥብ ያገኙበትን ድል ማስመዝገብ ችለዋል።

 

በሊጉ ከመጨረሻ ደረጃ አንድ ደረጃ ከፍ ብሎ በመገኘት በአዲስ አበባ ስታዲየም ድሬደዋን ያስተናገደው ኢትዮ ኤሌትሪክ 1ለ0 በሆነ ውጤት ነው ያሸነፈው። ግቧንም በ46ኛው ደቂቃ ውጤቱ ለአሰልጣኙም ሆነ ለቡድኑ እፎይታን የሰጠ ነበር።


የኤሌትሪክ የሰኞ እለቱ ውጤት በጫና ውስጥ የቆዩትን አሰልጣኙን ተስፈኛ ሲያደርግ፤ ክለቡንም ለቀጣይ ውጤት የሚያነሳሳ ነው። ክለቡ 15 ጨዋታ ካደረገት አርባምንጭና ድሬደዋ ከነማ እኩል 13 ነጥብ ይዞ 14ኛ ላይ ይገኛል። ተሸናፊው ድሬደዋ ከነማ እኩል 13 ነጥብ ቢኖረውም በግብ ክፍያ ልዩነት ተሽሎ 13ኛ ደረጃን ለመያዝ ችሏል። ወልዲያ በ11 ጨዋታ11 ነጥብ ይዞ የመጨረሻውን 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።


ፕሪሚየር ሊጉን ደደቢት በ13 ጨዋታ አድርጎ 28 ነጥብ እየመራ ነው። 15 ጨዋታዎችን ያደረገው መቀለ ከተማ እና አዳማ ከተማ በ25 እና 23 ነጥብ ሁለተኛና ሶስተኛ ናቸው።


ሻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ13 ጨዋታ 22 ነጥብ ይዞ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ደደቢት በ13 ጨዋተዎች 28 ነጥብ ሊጉን በመምራት ላይ ይገኛል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
67 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 537 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us