አሰልጣኝ ጸጋዬ በአመት ውስጥ ሶስተኛ ክለብ ይዘዋል

Wednesday, 21 February 2018 12:21


የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሰልጣኞች በፍጥነት የሚቀያየሩበት ሆኗል። ለረጀም አመታት መቆየትአልቻሉም። አንደኛው ዙር ሳይጠናቀቅ ከአራት በላይ አልጣኞች ተሰናብተዋል። ሊጉ አንደኛው ያሰናበተውን ሌላው ፈጥኖ የሚቀበልበትም ሆኗል።


አሰልጣኝ ጸጋዬም ከአንዱ ክለብ ወደ ሌላው በመዘዋወር ዋነኛው ተጠቃሽ ሆነዋል። አሰልጣኙ በአንድ አመት ውስጥ ሶስት ክለብን በማሰልጠን ተጠቃሽ ያደረጋቸው የታሪክ አጋጣሚ ዘንድሮ ተፈጥሯል።
የዛሬ አመት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰልጣኝ የነበሩት ጸጋዬ ኪዳነማሪያም በሊጉ መጠናቀቂያ አካባቢ ከክለቡ ጋር መለያየተቻው ይታሰወሳል። ቡድኑ ደካማ ውጤት በማስመዝገቡ ከፕሪሚየር ሊጉ ወረደ። ቡድኑም እንዲፈርስ ተደረገ።


አሰልጣኝ ጸጋዬ ከኢትጵዮያ ንግድ ባንክ ከተለያዩ በኋላ ከአራት ወር በኋላ አርባምንጭ ከተማን ተረከቡ። በደቡቡ ክለብም ያልተሳካ ጊዜ ነው ያሳለፉት። በተከታታይ ነጥብ መጣላቸውን ተከትሎ ከደጋፊዎች ከፍተኛ ጫና ገጠማቸው። ለስድስት ወር ብቻ ቆይተው ከአንድ ወር በፊት ከክለቡ መለያየታቸው ተሰምቷል።


ከአርባምንጭ በኋላ ቀጣይ ማረፊየቸው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ እግር ኳስ ሆኗል። አሰልጣኙ በክለቡ ለአንድ አመት የሚያቆያቸውን ስምምነት መፈረማቸውም ተሰምቷል። ይህም አሰልጣኙን ባለፉት አንድ አመት ውስጥ ሶስት የሊጉን ክለቦች በማሰልጠን የመጀመሪያው ሆነዋል።


አሰልጣኝ ጸጋዬ ለረጅም ጊዜ የቆዩት በሐረር ቢራ ክለብ ነበር። በምስራቁ ክለብ ለሰባት አመታት ነበር የቆዩት። ከሐረር ቢራ ቀጥለው በንግድ ባንክ ከዚያም የኤሌትሪክን ክለብ፤ ለጥቂት ጊዜም የኢትዮጵያ ቡናን ክለብ አሰልጥነዋል።


ላለመውረድ የሚጫወቱ ክለቦችን ጋር ያልተሰካ ጊዜን በማሳለፍ የሚታወቁት አሰልጣኝ ጸጋዬ አሁንም በውጤት ቀውስ ውጥ የሚገኘውን ወልዋሎን ለመታደግ ከፍተኛ የቤት ስራ ይጠብቃቸዋል።


ዘንድሮ ፕሪሚየር ሊጉን የተቀላቀለውን ወልዋሎ አጀማመሩ መልካም ቢመስልም በተከታታይ አስር ጨዋታዎች ማሸነፍ ተስኖታል። ከብሔራዊ ሊግ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ያሳደገውን አሰልጣኝ ብርሃኔ ገብረእግዚአብሔርን በማሰናበት ጸጋዬነ ለመቅጠር ተገዷል።


ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ በ15 ጨዋታ 13 ነጥብ ይዞ 10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
68 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 792 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us