ዛማሊክ ወላይታ ዲቻ ላለበት ጨዋታ 25ሺ ደጋፊዎቹ ስታዲየም እንዲገቡ ጠይቋል

Wednesday, 28 February 2018 13:04

 

በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ቅድመ ማጣሪያ የታንዛኒያውን ክለብ ዚማማቶን በደርሶ መልስ ያሸነፈው ወላይታ ዲቻ በቀጣዩ ማጣሪያ ከግብጹ ዛማሌክ ጋር ተገናኝቷል። ዛማሌክ በሜዳው በሚያደርገው ጨዋታ 25ሺ ደጋፊዎቹ ስታዲየም እንዲገቡ ፈቃድ ጠይቋል።


ካፍ ባወጣው መርሀ ግብር መሰረት የወላይታ ዲቻና ዛማሌክ ጨዋታ የመጀመሪያው ጨዋታ ማርች 7 ቀን ነው። የመልሱ ደግሞ በስዊዝ ከተማ አርሚ ስታዲየም እንደሚካሔድ ታውቋል። ወላይታ ዲቻ ከጠንካራ ክለብ ቢመደብም በሜዳው የሚያደርገውን ጨዋታ በሰፊ የግብ ልዩነት ማሸነፍ ካልቻለ በመልሱ ጨዋታ ከፍተኛ ጫና እንደሚገጥመው መናገር ይቻላል።


የመልስ ጨዋታውን በሜዳው የሚያደርገው ዛማሌክ በበኩሉ 25ሺ ደጋፊዎቹ በስታዲየም ተገኝተው እንዲደግፉት የግብጽ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ጠይቋል። ክለቡ ጨዋታውን የሚያደርገው ከካይሮ ከተማ 125 ኪ.ሜ ከምትርቀው ስዊዝ ከተማ በመሆኑ ጥያቄው ተቀባይነት ሊያገኝ እንደሚችል ይጠበቃል።


የግብጽ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ2012 በአል አህሊና በአል ማስሪ ጨዋታ ከ72 በላይ ደጋፊዎች ለሞት ካበቃው ክስተት በኋላ ክለቦች ያለ ደጋፊዎች በባዶ ስታዲየም እንዲጫወቱ ማገዱ ይታወሳል። ይህንን እገዳ አንስቶ የነበረ ቢሆንም ከ20 በላይ የሰዎች ህይወት በመጥፋቱ እንደገና እገዳውን ለማጽናት ተገዷል። ዘንድሮ ደግሞ ይህ እገዳ በከፊል ተነስቶ ክለቦቹ በአለምአቀፍ ጨዋታዎች ላይ ብቻ ደጋፊዎች በስታዲየም እንዲገኙ ፈቅዷል። የደጋፊዎች ቀጥር ላይም ገደብ አድርጓል።


እንደ አል አህሊ ያሉ በግብጽ ዋና ከተማ ካይሮ በሚገኙ ስታዲየሞች የሚጫወቱ ክለቦች በገደብ ደጋፊዎች እንዲታደሙ ነው የተፈቀደው። አል አህሊ በነበረው ጨዋታ 5 ሺ ደጋፊዎች ብቻ እንዲታደሙ ነው የተፈቀደለት። ለዚህም ደግሞ ዋንኛ ምክንያቱ በዋና ከተማዋ ህዝብ ከፍተኛ ስለሆነ በስታዲየም የሚፈጠሩ ረብሻዎችንን ለመቆጣጠር አዳጋች መሆኑ ነው ተብሏል።


ዛማሌክ ባለፈው አመት በግብጽ ፕሪሚየር ሊግ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቁ ነበር የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ መሆን የቻለው። በዘንድሮው የሀገሪቱ ፕሪሚየር ሊግ ባደረጋቸው 26 ጨዋታዎች 48 ነጥብ ይዞ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ነው። 18 ከለቦች የሚሳተፉበትን የግብጽ ፕሪሚየር ሊግን አል አህሊ በ69 ነጥብ እየመራ ይገኛል።
ወላይታ ዲቻ ደግሞ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማክሰኞ እለት ከጅማ አባ ጅፋር ጋር ያደረገውን ተስተካካይ ጨዋታ ውጤት ሳይጨምር በ13 ጨዋታዎች 16 ነጥቦችን ይዞ 9ኛ ደረጃን ይዟል።

 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
95 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 638 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us