የበርሚንግሀም የአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ነገ ይጀምራል

Wednesday, 28 February 2018 12:23

 

 

በየሁለት አመቱ የሚካሔደው የአለም የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ነገ ሐሙስ በእንግሊዟ በርሚንግሀም ከተማ ይጀመራል። ለሁለት የወርቅ ሜዳልያ ተዘጋጅቻለሁ ያለችው ገንዘቤ ዲባባ የመጀመሪያውን ሜዳልያ በእለቱ በሚካሔደው የ3,000 ሜትር ፍጻሜ ላይ እንደምታገኝ ይጠበቃል።


ለ17ኛ ጊዜ የሚካሔደው የአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ነገ በድምቀት ተጀመረ። ለአራት ቀናትም ሲካሔድ ይቆያል። በውድድሩ ተሳታፊ የሆነችው ኢትዮጵያ ሜዳልያ ከምትጠብቅባቸው ርቀቶች አንዱ የሆነው የሴቶች የ3.000 ሜትር ፍፃሜ ሩጫ ይካሔዳል። በርቀቱም ገንዘቤ ዲባባ የአሸናፊነት ግምት ተሰጥቷታል።


ከገንዘቤ በተጨማሪ ዳዊት ስዩምና ፋንቱ ወርቄ በርቀቱ የሚሳተፉ ሲሆን፤ ጠንካራ ፉክክር በማድረግ ለኢትዮጵያ ከአንድ በላይ ሜዳልያ ሊያመጡ እንደሚችሉ ይጠበቃሉ። በተለይም ደግሞ በውድድሩ ሁለት የወርቅ ሜዳልያ የማስመዝገብ እቅድ እንዳላት ተናግራ የነበረችው ገንዘቤ ዲባባ አንደኛውን የወርቅ ሜዳልያ እንደምታገኝ ይጠበቃል።


ገንዘቤ ከ3.000 ሜትር በተጨማሪ በ1500 ሜትርም እንደምትወዳደር ይታወቃል። አትሌት ዳዊት ስዩምም በተመሳሳይ በሁለቱም ርቀቶች ከገንዘቤ ጋር ጠንካራ ፉክክር እንደምታደርግ የምትጠበቅ አትሌት ናት።


በውድድሩ ሁለተኛ ቀን አርብ እለት የወንዶች የ3.000 ሜትር ማጣሪያ የሚደረግ ሲሆን፤ ሐጎስ ገብረህይወት፣ ዮሚፍ ቀጀልቻና ሰለሞን ባረጋ ኢትዮጵያን ወክለው ይሮጣሉ። ወጣቱ አትሌት ሰለሞን ባረጋ ልምድ ካላቸው የሀገሩ አትሌቶች ጋር ተፎካክሮ አስደናቂ ውጤት ሊያስመዘግብ እንደሚችል የቅርብ ጊዜ ውጤቶቹ ይመሰክራሉ። ከ20 አመት በታች የአለም ወጣቶች ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳልያ ባገኘበት በ3000 ሜትር ርቀት ምርጥ ብቃቱን እንደሚያሳይም ግምት ተሰጥቶታል።


መሀመድ አማን ብቸኛው የኢትዮጵያ አትሌት ሆኖ በቀረበበት በወንዶች የ800 ሜትር ሩጫ የማጣሪያ ውድድር አርብ እለት የሚደረግ ሲሆን፤ የፍጻሜ ፉክክሩ ደግሞ ቅዳሜ ይካሔዳል። በተመሳሳይ ርቀት በሴቶች ከኢትዮጵያ አትሌት ሀብታም አለሙ ብቻ የቀረበች ሲሆን፤ ቅዳሜ እለት የማጣሪያ ውድድሯን ታደርጋለች። እሁድ እለትም የርቀቱ የፍጻሜ ፉክክር ይደረጋል።


በሶስተኛው የውድድሩ ቀን ቅዳሜ እለት ገንዘቤ ዲባባ የምትጠበቅበት የ1.500 ሜትር የፍጻሜ ፉክክር ይደረጋል። ገንዘቤ የአለም ክብረወሰንን በያዘችበት በዚህ ርቀት ተፎካካሪዎቿን በቀላሉ እንደምትረታ ግምት ተሰጥቷታል። በእለቱ በተመሳሳይ ርቀት የወንዶች የማጣሪያ ሩጫ የሚካሔድ ሲሆን፣ አማን ወጤ እና ሳሙኤል ተፈራ ብቻ ተሳታፊ ሆነው ቀርበዋል።


በሻምፒዮናው የመጨረሻው ቀን እሁድ ከሚካሔዱ የፍጻሜ ውድድሮች መካከል ኢትዮጵያ ሜዳልያ የምትጠብቅበት የወንዶች የ3000 ሜትር አንደኛው ነው። ከዚህ በተጨማሪም የሴቶች የ800 ሜትር የፍጻሜ ሩጫ ይከናወናል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
64 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 433 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us