ትውልደ ኢትዮጵያዊው አሰልጣኝ በእስራኤል ሊግ

Wednesday, 28 February 2018 13:12

 

በእስራኤል እግር ኳስ ክለቦች በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ተጫዋቾች ቢገኙም በአሰልጣኝነት ግን የጎላ ስኬት ያስመዘገበ የለም። በቅርቡ ግን መሳይ ደጎ የተባለ ትውልደ ኢትዮጵያዊ አሰልጣኝ በእስራኤል ፕሪሚየር ሊግ በአሰልጣኝነት በመቅረብ በሀገሪቱ እግር ኳስ አዲስ የተባለ የስኬት ታሪክ ማስመዝገብ ችሏል። መሳይ በፕሪሚየር ሊጉ በዋና አሰልጣኝነት የተቀጠረ የመጀመሪያው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ለመሆንም በቅቷል።


አዲስ አበባ ተወልዶ ያደገው መሳይ ወደ እስራኤል ከቤተሰቦቹ ጋር የሔደው በ1990 እ.አ.አ. ነበር። በእስራኤል የተለያዩ ክለቦች እግር ኳስን ሲጫወት የቆየ ሲሆን፤ በጉዳት ጫማውን ለመስቀል ተገዷል። ይሁንና ከሚወደው እግር ኳስ ስፖርት ጨርሶ አልራቀም። ከ2013 ጀምሮ የግል ስራውን እየሰራ የአሰልጣኝነት ሙያን ይማር ነበር። በግሉም የፔፕ ጋርዲዮላ አድናቂ ሲሆን፤ የእርሱን የስልጠና ልምምዶች በቪዲዮ በመመልከት ብዙ እውቀት እንዳገኘ ይናገራል።


በአሰልጣኝት የመጀመሪያ ክለቡ ለታችኛው ሊግ የሚጫወተው ሀፖል ክፋር የተባለው ክለብ ነው። ከሁለት አመት በፊት በ2016 በክለቡ በምክትል አሰልጣኝነት የተቀጠረ ሲሆን፤ ዋናው አሰልጣኝ ሲሰናበት እሱን ተክቶ ክለቡን ለአንድ አመት ድረስ አሰልጥኗል።


ባለፈው አመት በድጋሚ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ የተመለሰው የአሽኬሎን ክለብ ዋና አሰልጣኝ መሰናበቱን ተከትሎ ያልተጠበቀ ጥሪ ደረሰው። በውጤት ቀውስ የሚገኘውን ክለብ ከወራጅነት ለመታደግ ፈታኝ ቢሆንም የቀረበለትን ጥሪ ተቀብሏል።


በእስራኤል ፕሪሚየር ሊግ የሚገኝ ክለብን በዋና አሰልጣኝነት በመምራት የመጀመሪያው ትውልደ አትዮጵያዊ ያደረገው ሀላፊነት ከባድ ቢሆም እንደሚወጣው እርግጠኛ ነው።


‹‹ለታችኛው ሊግ የሚጫወተው የሃፖል ክፋር ሳባ ክለብን ሳሰለጥንም ሀላፊነቱ ከባድ ነበር። አሁንም የተሰጠኝ ሀላፊነት በተመሳሳይ መልኩ ነው የምመለከተው። ከባዱን ፈተና እንደምወጣው እርግጠኛ ነኝ። ለዚህም ነው ሀላፊነቱን የተረከብኩት›› ብሏል።


የመሳይ ታናሽ ወንድም ባሩች ደጎ በእስራኤል የእግር ኳስ ተጫዋች ሲሆን፤ በፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ ለሆነው ማካቢ አይረን አሽዶድ ለተባለ ስመጥር ክለብ ይጫወታል። ከዚህ በፊት ለማካቢ ቴል አቪቭ፣ ሃፖል ቴልአቪቭ እና ሃፖል አሽኬሎን ተጫውቷል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
95 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 480 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us