ዩሴን ቦልት ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋች ሆኗል

Wednesday, 28 February 2018 13:15


በአትሌቲክስ ስፖርት አይረሴ ያደረገውን ድል ያስመዘገበው ጃማይካዊው ዩሴን ቦልት አሁን ደግሞ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋች መሆኑን በይፋ አውጇል። ‹‹ለእግር ኳስ ክለብ ፈርሜያለሁ›› ሲልም ሰኞ እለት ተናግሯል።


በ2017 በለንደን አለም ሻምፒዮና የሩጫው አለምን በይፋ የተሰናበተው ቦልት፤ ቀድሞ እንደተናገረው ራሱን በእግር ኳስ ስፖርት ተፎካካሪ ለማድረግ ሲዘጋጅ ቆይቷል። ከሳምንታት በፊት ከደቡብ አፍሪካው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ክለብ ጋር ልምድ ሲሰራ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፤ በጀርመኑ ቦርሲያ ዶርትሙንድም የቀረበለትን ግብዣ ተቀብሎ እንደሚለማመድ ሲጠበቅ ነበር። ይሁንና ጃማይካዊው ባልተጠበቀ ጊዜ ለፕሮፌሽናል ክለብ ለመጫወት መፈረሙ ነው የተሰማው።


የ31 አመቱ ቦልት የእግር ኳስ ተሰጥኦ እንዳለው ቢታወቅም ሩጫን ካቆመ በጥቂት ጊዜ ውስጥ የእግር ኳስ ክለብ ተጫዋች ይሆናል ተብሎ አልተገመተም ነበር። ሰሞኑን በትዊተር ገጹ በቪዲዮ በለቀቀው መረጃ ላይ ለእግር ኳስ ክለብ ለመጫወት መፈረሙን አስታውቋል።


‹‹ለእግር ኳስ ክለብ ለመጫወት ፈርሜያለሁ። ሲል የተናገረው ቦልት፤ ለየትኛው ክለብ እንደፈረመ ግን አላሳወቀም። በርካቶችም ግምታቸውን በመስጠት ተወያይተውበታል። የአብዛኞች ግምት ልምምድ ሲሰራ የቆየበት የደቡብ አፍሪካው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ላይ አርፏል።


ቦልት ከልቡ ለሚደግፈው ለማንቸስተር ዩናይትድ የመጫወት ፍላጎት እንዳለው በተደጋጋሚ መናገሩ ይታወሳል። በጆዜ ሞሪንሆ የሚመራው ቡድን ግን የቀድሞውን ሯጭ ለማስፈረም ምንም አይነት ፍላጎት አለማሳየቱ ግምቶች ሁሉ ለደቡብ አፍሪካው ክለብ ሆነዋል።


የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ክለብም በትዊተር ገጹ ላይ ጃማይካዊውን እንዳስፈረመ ፍንጭ የሚሰጥ መልዕክት መጻፉ ግምቶችን ለእውነታነት የቀረቡ አድርጓቸዋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
109 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 450 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us