የመሐመድ ሳላህ ዋጋ በፍጥነት አሻቅቧል

Wednesday, 14 March 2018 13:15

 

ዘንድሮ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ድንቅ ብቃት እያሳየ የሚገኘው ግብጻዊው መሐመድ ሳላህ የሽያጭ ዋጋው በየጊዜው እያሻቀበ ነው። ባለፉት ስድስት ወራት በአውሮፓ ታላቅ ሊጎች ከሚጫወቱ ስመጥር ተጫዋቾች በፍጥነት ያሻቀበው ዋጋ የመሀመድ ሳላህ መሆኑን አዲስ ጥናት ይፋ አድርጓል።

የ2017 የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ የተሸለመው መሀመድ ሳላህ በፕሪሚየር ሊጉ ስኬታማ ጊዜን እያሳለፈ ይገኛል። የተጫዋቾች የዝውውር ሒሳቡም ከ74.7 ሚሊዮን ዩሮ ወደ 168.2 ሚሊዮን ዩሮ ከፍ ብሏል።

የሊቨርፑሉ አጥቂ ሳላህ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 24 ግቦችን በማስቆጥር የኮከብ ግብ አግቢነቱን መሪነት መያዝ ችሏል። ለክለቡም ሆነ ለሀገሩ ብሔራዊ ቡድን አሸናፊነት ወሳኝ የሆኑ ግቦችን በማስቆጠር ወሳኝነቱን አሳይቷል።

ሲ አይ ኢ ኤስ (CIES) የተባለ ተቋም ሰሞኑን ይፋ ባደገረው የተጫዋቾች የዝውውር ዋጋ ግምት ጥናት መሰረት ከፍተኛ ዋጋ ካላቸው 10 ተጫዋቾች መካከል ስድስቱ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ይገኛሉ። በአንደኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ደግሞ የግብጽ ብሔራዊ ቡድንና የሊቨርፑሉ ወሳኝ ተጫዋች መሐመድ ሳላህ ነው። ባለፈው አመት የተጫዋቹ የዝውውር ዋጋ 88.1 ሚሊዮን ዩሮ መሆኑን ይፋ አድርጎ ነበር። በአመቱ ደግሞ የተጫዋቹ ዋጋ 168.2 ሚሊዮን ዋጋ አሻቅቦ ተገኝቷል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
94 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 540 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us