15ኛው ቅድሚያ ለሴቶች ሩጫ በድምቀት ተከናወነ

Wednesday, 14 March 2018 13:16

 

አመታዊውን አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ምክንያት በማድረግ የሚዘጋጀው የቅድሚያ ለሴቶች የ5ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ለ15ኛ ጊዜ በድምቀት ተከናውኗል። በአትሌቶች መካከል በተካሔደው ፉክክር ጸሐይ ገመቹ አሸንፋለች። በተምሳሌት ሴቶች ፉክክርን አርቲስት አምለሰት ሙጬ በቀዳሚነት አጠናቃለች።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 15ኛው ቅድሚያ ለሴቶች የጎዳና ላይ ሩጫ እሁድ እለት መነሻና መድረሻውን በአትላስ አካባቢ አድርጎ ተካሒዷል። የሩጫ መድረኩ 15ኛ ክብረ በአልም በመሆኑ በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀ ነበር። በመሮጫ መንገዶች ላይ አዝናኝ የሙዚቃ ዝግጅቶች ተከናውነዋል።

‹‹ከጥቃት ነጻ ህይወት መብቴ ነው›› የሚል መሪ ቃልን ይዞ የተከናወነው የዘንድሮው ቅድሚያ ለሴቶች ሩጫ ላይ ከ12,000 በላይ ተሳታፊዎች ተካፋይ ነበሩ። ለመጀመሪያ ጊዜም ከኡጋንዳ ሁለት አትሌቶች በተጋባዥነት ተፎካካሪ ሆነው ቀርበዋል።

በአትሌቶች መካከል የተካሔደውን ፉክክር ያሸነፈችው ጸሐይ ገመቹ ርቀቱን 16፡05፡12 ነው ያጠነቀቀችው። ሁለተኛ ደረጃን ያገኘችው ደባሽ ከላል 16፡09፡16 የገባች ሲሆን፤ ሶስተኛ ሆና የገበችው የኔነሽ ጥላሁን ርቀቱን 16፡09፡48 አጠናቃለች። ከ110 በላይ አትሌቶች በተሳተፉበት ፉክክር አሸናፊዋ አትሌት ጸሐይ የ15,000 ብር ተሸላሚ ስትሆን፤ እስከ 10ኛ ደረጃን ይዘው ላጠናቀቁ አትሌቶች እንደየደረጃቸው የገንዘብ ተሸላሚ ሆነዋል።

በተለያዩ ሙያዎች በተምሳሌትነት የሚጠቀሱ ሴቶች በተፎካከሩበት የተምሳሌት ሴቶች ፉክክር ዘንድሮ ለአምስተኛ ጊዜ ተካሒዷል። የ5ኪሎ ሜትር የተምሳሌት ሴቶች ፉክክርን አርቲስት አምለሰት ሙጬ በቀዳሚነት አጠናቃለች። የሴቶች እግር ኳስ ቡድን አሰልጣኝ መሰረት ማኔ ሁለተኛ ደረጃን ስታገኝ፤ የጃኖ ባንድ ሴት ሙዚቀኞች ሀሌሉያ እና ሔዋን ሶስተኛ ሆነዋል። ከሩጫው አምባሳደር መሰረት ደፋር እጅም የእውቅናና ምስጋና የምስክር ወረቀትና የማስታወሻ ስጦታ ተቀብለዋል።

በሩጫ መድረኩ ላይ መሪ ቃሉን መሰረት ያደረጉ መልዕክቶች የተላለፉ ሲሆን፤ በአዝናኝ ዝግጅቶች በመታጀብ አላማው ግቡን እንዲመታ ተደርጓል። የጃኖ ባንድ ሴት የሙዚቃ አባላትና ድምጻዊቷ ሔለን በርሔ እንዲሁም ሴት ዲጄዎች ታዳሚውን በሙዚቃ ስራዎቻቸው ሲያዝናኑ ቆይተዋል። ከጃማይካ የመጣችው ሙዚቀናዋ ጆይ ማክም በመድረክ ላይ የሬጌ ስራዎቿን በማቅረብ ታዳሚውን አዝናንታለች።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
73 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 514 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us