ቅዱስ ጊዮርጊስ በካምፓላ ወሳኙን ጨዋታ ያደርጋል

Wednesday, 14 March 2018 13:18

 

የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ከዩጋንዳው ክለብ ኬሲሲኤ ጋር የመልስ ጨዋታውን ያደርጋል። የኡጋንዳው ክለብ በሜዳው ያለመሸነፍ ታሪክ ለማስመዝገብ እንደሚዘጋጅ አሰልጣኙ ተናግረዋል።

ባለፈው ሳምንት ሐሙስ በአዲስ አበባ ስታዲየም ደጋፊዎቹ በልዩ የሽብርቅ ጥበብ ተውበው ቢገኙም የሜዳው ውስጥ ውጤት ግን የሚያስከፋ ነበር። ጨዋታው ምንም ግብ ሳይቆጠርበት በአቻ ውጤት መጠናቀቁ ለጊዮርጊስ የመልስ ጨዋታውን ፈታኝ የሚያደርግበት ይሆናል።

የሁለቱ ክለቦች የመልስ ጨዋታ ማርች 17 ቀን የሚካሔድ ሲሆን፤ ካምፓላ የሚገኘው ሉጎጎ ስታዲየም ይከናወናል። የኡጋንዳው ክለብ 10,000 ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ባለው ስታዲየም የሚያደርገውን የመልስ ጨዋታ ለማሸነፍ ከፍተኛ ዝግጅት ማድረጉን አስተውቋል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በአቻ ውጤት የተጠናቀቀው ጨዋታ ለኡጋንዳዎች ከፍተኛ ደስታን ያጎናጸፈ ሲሆን፤ የቡድኑ አሰልጣኝ ማይክ ሙቴቢ የመልሱን ጨዋታ ያለ ጫና እንዲጫወቱ የሚያስችላቸው መሆኑን ተናግረዋል።

‹‹ከሜዳችን ውጪ ባደረግነው ጨዋታ ግብ አለማስቆጠራችን የመልሱ ጨዋታን ከባድ ያደርግብናል። ቢሆንም የምንጫወተው በሜዳችን እና በደጋፊያችን ፊት ስለሆነ ያለ ጫና እንሸንፋለን›› ሲሉ ተናግረዋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ በውድድሩ መድረክ የተሻለ የተሳትፎና ነው ያለው። ዘንድሮም ካለፋው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ክለቡ ተዘጋጅቷል። አሰልጣኙም ለመልሱ ጨዋታ በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር እንደሚያልፉ ነው የተናገሩት።

በውድድሩ 16 ክለቦች ወደ ሚሳተፉት ሩብ ፍጻሜ መድረስ የቻለ ክለብ የ550,000 ዶላር ሽልማት ከካፍ የሚቀበል ይሆናል። በቀጣዩ ማርች 17 የሚካሔደውን የመልስ ጨዋታ ያሸነፈ ክለብ ገንዘቡን ያገኛል። ውጤቱ ባደገ ቁጥርም ገንዘቡም እያደረገ ይሔዳል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ባለፈው አመት በቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎው ለምድብ ማጣሪያ ጨዋታ በማለፍ የ550,000 ዶላር ሽልማት ማግኘቱ ይታወሳል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
67 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 385 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us