ወላይታ ዲቻ የሐዋሳ ድሉን ለማስጠበቅ ወደ ካይሮ ያቀናል

Wednesday, 14 March 2018 13:20

 

በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ የሆነው የወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ክለብ ከዛማሌክ ጋር የሚኖረው የመልስ ጨዋታ ፈታኝ እንደሚሆን ይጠበቃል። የቡድኑ አሰልጣኝ ዘነበ ፍሰሀ የመልስ ጨዋታውን በጥንቃቄ እንጫወታለን ሲሉ፤ የግብጹ አቻቸው ደግሞ በሜዳችን የምናደርገውን ጨዋታ እናሸንፋለን በማለት በእርግጠኝነት ተናግረዋል።

ወላይታ ዲቻ ባለፈው ሳምንት በሐዋሳ ስታዲየም የግብጹን ዛማሌክ ቡድንን አስተናግዶ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወሳል። በመጀመሪያው አጋማሽ በዛብህ መለዮ አማካኝነት ግብ በማስቆጠር መምራት የቻለው ዲቻ በተከላካይ ስህተት የተቆጠረችበት አንዲት ግብ ቡድኑን ዋጋ የምታስከፍልና የምታስቆጭ ነበረች። ከእረፍት መልስ በያሬድ ዳዊት ሁለተኛ ግብ በማስቆጠር ቡድኑ በሜዳውና በደጋፊው ፊት የግብጹን ሀያል ክለብ በማሸነፍ ለክለቡ አዲስ የድል ታሪክ አስመዝግቧል።

‹‹ኳስ ተቆጣጥረን በመጫወታችን ነው ያሸነፍነው›› በማለት የግብጹን ክለብ እንዴት እንዳሸነፉ የተናገሩት አሰልጣኝ ዘነበ ፍሰሀ፤ በመልሱ ጨዋታም ተመሳሳይ የጨዋታ ዘይቤ ተጋጣሚያቸውን እንደሚገጥሙ ይጠበቃል።

የዛማሌኩ አሰልጣኝ ኢሀብ ጋላል በበኩላቸው በሜዳቸው የሚያደርጉትን የመልስ ጨዋታ በሰፊ የግብ ልዩነት እንደሚያሸንፉ በእርግጠኝነት ተናግረዋል። በሐዋሳ ስታዲየም ለመሸነፋቸውም የሜዳውን ምቹ አለመሆን በምክንያትነት ጠቅሰዋል።

‹‹የሐዋሳ ስታዲየም ሜዳው ኳስን በአግባቡ ተቆጣጥረን እንዳንጫወት አድርጎናል። በእንደዚያ አይነት ሜዳ ላይ ኳስን ለመጫወት በጣም ነው ያስቸገረን። ግቦች የተቆጠሩብንም በሜዳው ምቹ አለመሆን ነው›› ሲሉ ለግብጽ ጋዜጦች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በስዊዝ ከተማ በሚካሄደው የመልስ ጨዋታም ደጋፊዎቻቸውን የሚያስደስት ውጤት እንደሚያመዘግቡ ነው የተናገሩት።

‹‹በእርግጠኝነት የመልሱን ጨዋታ እናሸንፋለን። ተጋጣሚያችን በአህጉራዊ ውድድሮች ላይ የተሳትፎ ልምድ ስለሌለውም ጭምር ለእኛ የሚፈትነን አይደለም›› በማለት ለወላይታ ዲቻ ቡድን ቀላል ግምት መስጠታቸውን የሚገልጽ አስተያየት ሰጥተዋል።

በመጀመሪያው ጨዋታ ጥሩ ሲንቀሳቀስ የነበረውና በዚህ ዓመት ክለቡን የተቀላቀለው ሃይማኖት ወርቁ በበኩሉ፤ “ዛማሊኮች ለእኛ የነበራቸው ግምት በጣም ዝቅተኛ ነበር። ጨዋታውን በማሸነፍም ግምታቸው ትክክል አለመሆኑን አሳይተናቸዋል። እነሱ ምንም እንኳን ትልቅ ክለብ ቢሆንም፤ ውጤታችንን አስጠብቀን ወደ ቀጣዩ ዙር ለመግባት ተዘጋጅተናል” ብሏል። አማካይ ተከላካዩ አያይዞም፤ ለዛማሊክ የተለየ ዝግጅት አለማድረጋቸውን ገልጾ “ሁሉም የቡድኑ አባላት ጨዋታውን ለማሸነፍ ቁርጠኛ ነው” ብሏል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
84 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 441 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us