ሙሉአለም ረጋሳ ለሐዋሳ ከተማ

Wednesday, 28 March 2018 13:01

በፕሪሚየር ሊጉ አንጋፋ ከሚባሉ ተጨዋቾች መካከል አንዱ የሆነው (ፕሪሚየር ሊጉ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ እየተጫወተ ያለ ብቸኛው ተጫዋች) የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አማካይ ሙሉአለም ረጋሳ አሁንም በድንቅ ብቃት እየተጫወተ ነው። ለክለብ መጫወት ካቆመ ከሁለት አመት በኋላ ፊርማውን ላኖረለት ለሐዋሳ ከተማ ወሳኝ ተጫዋችነቱን በማሳየት ላይ ነው። በሊጉ ሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ ሐዋሳዎች ሶስት ነጥብ እንዲያገኙ ያደረገች ግብ ማስቆጠር ችሏል።


ሙሉአለም የእርሱ ዘመን ተጨዋቾች ጫማቸውን በሰቀሉበት ጊዜ አሁንም በአማካይ ቦታ ድንቅ ተጫዋችነቱን በማሳየት ላይ ነው። ለግቦች የተመቻቹ ካሶችን በማቀበልም ሆነ ግቦችን በማስቆጠር አሁንም ያላበቃ ተሰጥኦውን በመግለጥ ላይ ነው። የፕሪሚየር ሊጉ ሁለተኛ ዙር ሲጀመርም ሐዋሳ አንድ ለባዶ ሲያሽንፍ ብቸኛዋን ግብ ያቆጠረው እርሱ ነበር።


አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ሙሉአለምን በቡድኑ ውስጥ ሲያካትት በርካታ ትችቶች ተሰንዝረውበት ነበር። እርሱ ግን በተጫዋቹ ላይ እምነት ነበረው። ተጫዋቹም አላሳፈረውም። ቡድኑ ውጤት ባስመዘገበባቸው ግጥሚያዎች ሁሉ የእርሱ የጎላ ሚና በተደጋጋሚ በማሳየት ላይ ይገኛል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
71 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 784 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us