ወላይታ ዲቻ በአሸናፊነቱ ቀጥሏል

Wednesday, 28 March 2018 13:02

 

በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን የግበጹን ሀያል ክለብ ዛማሌክን በመጣል አዲስ ታሪክ ያስመዘገበው ወላይታ ዲቻ በሊጉም አሸናፊነቱን ቀጥሏል። የሊጉን መሪ ደደቢትን 1ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ደረጃውንም ማሻሻል ችሏል።


ከአህጉራዊ መድረክ መልስ የአሸናፊነት ስነልቦናን መገንባት እንደቻለ የሚታመነው ወላይታ ዲቻ ባፈው ሰኞ በሜዳው ያደረገውን የሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ በአሸናፊነት አጠናቋል። ኮከብ ግብ አግቢውን ጌታነህ ከበደን ከቅጣት መልስ ካሰለፈው ከደደቢት ጋር ያደረገውን ጠንካራ ጨዋታ በአምሬላህ ደልታታ ብቸኛ ግብ ነው ያሸነፈው።


የአምናው የሊጉ አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ ተጉዞ ከድሬደዋ ከተማ ጋር ያደረገውን ጨዋታ ያለግብ በአቻ ውጤት ነው ያጠናቀቀው።


ጊዮርጊስን በሜዳው ያስተናገደው ከወራጅነት ቀጠና ያልተላቀቀው ድሬደዋ ከተማ በ14 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።


ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ ከሲዳማ ጋር ያደረገውን ጨዋታ ሶስት ነጥብ ይዞ መመለስ ችሏል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ አንድ ለባዶ በሆነ ውጤት ነበር የተጠናቀቀው። ግቧንም የፊት መስመር ተጫዋቹ ሳሙኤል ሳኑሚ በ59ኛ ደቂቃ ላይ ነው ያስቆጠረው።


መቀሌ ከተማ በሜዳው አርባ ምንጭ ከተማን 4ለ0 ሲያሸንፍ፤ ወልዲያን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም አዳማ ላይ ያስተናገደው አዳማ ከተማ 3ለ1 አሸንፏል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
59 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 775 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us