ወላይታ ድቻ በድጋሚ በካይሮ ይጠበቃል

Wednesday, 28 March 2018 13:06

በቅርቡ የዛማሌክን እግር ኳስ ቡድን በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ በደርሶ መልስ ያሸነፈው ወላይታ ድቻ በመረብ ኳስ ቡድኑም በተመሳሳይ ከተማ በካይሮ ለውጤት ይጠበቃል። የአፍሪካ የክለቦች መረብ ኳስ ውድድር በግብጽ አስተናጋጅነት በካይሮ ከተማ ትናንት ማክሰኞ እለት ተጀምሯል።


የእግር ኳስ ቡድኑ ከፍተኛ አድናቆት ያስገኘለትን ውጤት ያስመዘገበው ወላይታ ድቻ ስፖርት ክለቡ በመረብ ኳስ ቡድኑም ውጤታማ እንደሚሆን ይጠበቃል።ወላይታ ድቻ በውድድሩ ላይ የሚሳተፈው ያለፈው አመት የኢትዮጵያ ቮሊ ቦል ሻምፒዮና አሸናፊ በመሆኑ ነው።


በአፍሪካ ቮሊ ቦል ኮንፌዴሬሽን አማካኝነት የሚዘጋጀው የክለቦች ሻምፒዮና ካይሮ በሚገኘው የአል አህሊ የስፖርት ማዕከል ውስጥ ይከናወናል። ሻምፒዮናው ማክሰኞ እለት የተጀመረ ሲሆን፤ ለአስር ቀናት ሲካሔድ ይቆያል። በውድድሩም ከሀያ የአፍሪካ ሀገሮች የተውጣጡ 23 የቮሊቦል ክለቦች ይሳተፋሉ። ግብጽ በአልአህሊ ኤ እና ቢ ቡድኖቿ፤ እንዲሁም በሳሙሀ ክለብ በሶስት ቡድኖቿ ተወክላ ትሳተፋለች።


በውድድሩ ላይ ከኢትዮጵያ የሚሳተፈው ወላይታ ድቻ በምድብ አራት ከካሜሮኑ ፖርት፣ ከአልጄሪያ ኦሊምፒክ፣ ከዩጋንዳው ካምፓላ፣ ከኬንያው ጂኤስዩ እና ከግብጹ ኤልጉይሽ ጋር ተደልድሏል። የመጀመሪያ ጨዋታውን መክፈቻው እለት ማክሰኞ ከካሜሮኑ ክለብ ጋር፣ ተጫውቷል። ዛሬ ረቡዕ ሁለተኛ ጨዋታውን ከኬንያው ክለብ ጋር ያደርጋል። ነገ ሐሙስ እለት ደግሞ ከዩጋንዳው ክለብ ጋር የሚጫወት ሲሆን፤ አርብ እለት ከኬንያው፣ እንዲሁም ቅዳሜ ከአልጄሪያው ክለብ ጋር እንደሚጫወት የወጣው የውድድሩ መርሀግብር ያመለክታል። ቡድኑ ከአምስቱ ክለቦች ጋር በሚያደርገው የምድብ ጨዋታዎች ላይ በሚያመዘግበው ውጤት መሰረትም በሻምፒዮናው የሚኖረው ቆይታ የሚወሰን ይሆናል።


በውድድሩ መድረክ የግብጹ አል አህሊ 12 ጊዜ በማሸነፍ የበላይነት አለው። የቱኒዝያው ክለብ አፍሪካን ኤንድ ሴፋክሲያን ስድስት ጊዜ ዋንጫውን በማንሳት በሁለተኛነት ተጠቃሽ ነው። ከምስራቅ አፍሪካ ኬንያ ብቻ ፕሪዝንስ በተባለው ቡድኗ አንድ ጊዜ ለፍጻሜ መድረስ ችላለች።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
75 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 628 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us