አትሌት ነፃነት ጉደታ የ15 ዓመት ክብረ ወሰን በመስበር ታሪክ ሰራች

Wednesday, 28 March 2018 13:08

በአትሌት ነጻነት ጉደታ በቫሌንሽያ ግማሽ ማራቶን ለ11 አመት የቆየ የግማሽ ማራቶን የአለም ክበረወሰን በመስበር ለአገሯ የወርቅ ሜዳሊያ ስታስመዘግብ ለግሏም የ50ሺህ ዶላር ተሸላሚ ሆናለች።

በየሁለት አመቱ የሚካሔደው የአለም የግማሽ ማራቶን ሻምፒዮና ባለፈው ቅዳሜ እለት በስፔን ቫለንሺያ በድምቀት ተካሒዷል። ከ80 በላይ ሀገሮች የተሳተፉበትን የውድድር መድረክ ኢትዮጵያ በበላይነት ማጠናቀቅ ችላለች። የኢትዮጵያ ቡድን በተናጥል በቡድንም የወርቅ ሜዳልያዎችን ወስዷል።


የኢትዮጵያ የግማሽ ማራቶን ቡድን በቫሌንሺያው ሻምፒዮና በሴቶች በተናጥል የወርቅ ሜዳልያ፤ በቡድን ደግሞ በሁለቱም ጾታ የወርቅ ሜዳልያ ወስዷል። ኢትዮጵያ ሶስት የወርቅ ሜዳልያዎችን በመውሰድ በአንደኛነት ነው ያጠናቀቀችው። ባለፉት አመታት የነበረውን የኬንያን የበላይነት በመስበሩም አድናቆት ተችሮታል።


በሰቶች መካከል በተካሔደው ፉክክር የአሸናፊነት ግምት የተሰጣቸው ስመ ጥር አትሌቶች የነበሩ ቢሆንም፤ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ነጻነት ጉደታ የአለም ክብረወሰን ጭምር በማሻሻል ነበር ያሸነፈችው። ያልተጠበቀ አሸናፊነት ያስመዘገበችው ነጻነት ርቀቱን 1፡06፡11 ማጠናቀቅ የቻለች ሲሆን፤ ቀድሞ በኬነያዊቷ አትሌት ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን በ11 ሰከንዶች ማሻሻል ችላለች።


ከነጻነት ጋር የተሰለፉት የኢትዮጵያ አትሌቶች ዘይነባ ይመር እና መሰረት በለጠ የአለም አቀፍ ልምድ የሌላቸው ወጣቶች ቢሆኑም ያስመዘገቡት ደረጃ የኢትዮጵያ ቡድን በነጥብ አንደኛ እንዲሆንና የወርቅ ሜዳልያ እንዲያገኝ አስተዋጽኦ አድርጓል።


የወንዶቹ ቡድን እንደጌታነህ ሞላና ጀማል ይመር ያሉ ልምድ ያላቸው አትሌቶችን ያካተተ ቢሆንም በተናጥል ሜዳልያ ውስጥ መግባት የቻለ አትሌት አልነበረም። ይሁንና አትሌቶቹ በውድድሩ ያስመዘገቡት የደረጃ ውጤት ኢትዮጵያ በወንዶቹም የቡድን የወርቅ ሜዳልያ እንድታገኝ አስችለዋል።


አትሌት ነጻነት በውድድሩ በተናጥል አሸናፊ በመሆኗ 30ሺህ ዶላር፤ የርቀቱን የአለም ክብረወሰን በመስበሯ ደግሞ ተጨማረ 50ሺህ ዶላር የምታገኝ ይሆናል። በቡድን የወርቅ ሜዳልያ ላስመዘገበው ለኢትዮጵያ ቡድን ከሚሰጠው የ15ሺህ ዶላርም ተካፋይ ትሆናለች።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
75 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 686 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us