ኢትዮጵያዊቷ ግብ ጠባቂ በቱርክ

Wednesday, 04 April 2018 14:12

 

በእግር ኳስ ስፖርት በውጭ ሀገሮች ሊግ ውስጥ የሚጫወቱ ኢትዮጵያውያን ወንድ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ቢኖሩም በሴቶች ግን ተመሳሳይ ታሪክ አናገኝም። በሴቶች እግር ኳስ የረጅም ጊዜ ታሪክ ያላት ኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ በሚጠቀስ ሊግ ውስጥ የመጫወት አጋጣሚ ያገኙ ተጫዋቾች የሏትም። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባል የሆነችው ዳግማዊት መኮንን ግን ይህንን ታሪክ የቀየረች ተጫዋች ሆናለች። በውጭ ሀገር የእግር ኳስ ክለብ መጫወት የቻለች የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ሆናለች።


ዳግማዊት መኮንን የመጀመሪያ ቆይታዋም በሀገሪቱ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ለሚወዳደረው አክዴኒዝ ነርሼሊክ ክለብ ነው። በክለቡ ቆይታዋ የምታሳየው ብቃት ታይቶ ለታዋቂው የቤሽኪሽታሽ ክለብ እንደምትዛወር ይጠበቃል።


በሴቶች እግር ኳስ ከጠንካራዎቹ የአውሮፓ ሀገሮች አንዷ የሆነችው ቱርክ በሁለተኛ ዲቪዚዮን ላይ እንኳን የሚደረጉ ፉክክሮች ጠንካራ ናቸው። ክለቦች ከተለያዩ ሀገሮች ተጫዋችን በማስፈረም ጭምር ለውጤታማነት የሚፎካከሩበት ነው። ዳግማዊት የምትገኝበት አክዴኒዝ ነርሼሊክ ክለብም አንደኛው ጠንካራ የሁለተኛ ዲቪዚዮን ክለብ ነው።


ረጅምና ግዙፍ ተክለሰውት ያላት ግብ ጠባቂዋ ዳግማዊት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከተጫወተችባቸው ክለቦች ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንዱ ነው። ተክለሀይማኖት ፔፕሲ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ደግሞ የተጫዋቿ የቀደመ መሰረት ነው። በእግር ኳስ ህይወቷ እስከ ብሔራዊ ቡድን የመሰለፍ የረጅም ጊዜ ልምድ ያላት ተጫዋች ናት።


ዳግማዊት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አንጋፋ ከሚባሉ ተጫዋቸች መካከል አንደኛዋ ናት። ለመጀመሪያ ጊዜ በኢንተርናሽናል የጨዋታ መድረኮች የተሰለፈችው ደግሞ እ.አ.አ. በ2004 ደቡብ አፍሪካ ባስተናገደችው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ነበር። በወቅቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ የነበረችው አለምነሽ አበበ ኢትዮጵያ ከናይጄሪያ ጋር የነበራትን ጨዋታ ከማድረጓ ከቡድኑ ተለይታ በመጥፋቷ ሁለተኛ ምርጫ የነበረችው ግብ ጠባቂ ዳግማዊት እንድትሰለፍ ነበር የተደረገው። እንደ ሰሚራ ከማልና አዲስ ፈለቀን የመሳሰሉ ተጫዋቾችን ያካተተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በውድድሩ የተሳትፎ ታሪኩ አራተኛ ደረጃ ነበር ያስመዘገበው።


ከደቡብ አፍሪካው የ2004 የአፍሪካ ዋንጫ በኋላ ዳግማዊት በተደጋጋሚ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመሰለፍ እድል አግኝታለች። በክለብ ደረጃም ከኢትዮጰያ ንግድ ባንክ ክለብ ጋር በተደጋጋሚ ዋንጫ ማንሳት ችላለች። የፍጹም ቅጣት ምቶችን በማዳን በኩል ደግሞ የተዋጣላት ናት። ንግድ ባንክ ለፍጻሜ በደረሰባቸው ጨዋታዎች የፍጹም ቅጣት ምቶችን በማዳን ሶስት ጊዜ ዋንጫዎችን አንስታለች።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
69 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 590 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us