አሰልጣኝ አጥናፉ ከሊጉ ተጫዋቾች ባለመምረጣቸው ተወቀሱ

Wednesday, 04 April 2018 14:14


 

የኢትዮጵያን ከ20 አመት በታች የወንዶች ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድንን የተረከቡት አሰልጣኝ አጥናፉ በመጀመሪያ ጨዋታቸው በሜዳቸው ሽንፈት ገጥሟቸዋል። አሰልጣኝኙ ለደረሰባቸው ሽንፈት ልምድ ያላቸው ተጫዋቾችን አለመምረጣቸው እንደሆነ የሚገልጹ አስተያየቶች ተሰንዝረዋል። እርሳቸው ግን ቡድናቸው ለደረሰበት ሽንፈት የተጋጣሚያቸው ቡድን ከእድሜ በላይ ተጫዋቾችን በማሰለፉ መሆኑን ነው የገለጹት።


ኒጀር ለምታስተናግደው ከ20 አመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታውን በሜዳው ከብሩንዲ ጋር የተጫወተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሜዳው የ2ለ0 ሽንፈት ደርሶበታል። በኢትዮጵያ ቡድን ሁለቱንም ግቦች ያስተናገደው በመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ ነበር። የመጀመሪያዋ ግብ የተቆጠረችው ጨዋታው በተጀመረ በሶስተኛው ደቂቃ ሲሆን፤ ሁለተኛዋ ደግሞ በ22ኛው ደቂቃ ላይ ነበር የተመዘገበችው።


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በጨዋታው በተደጋጋሚ ወደ ተጋጣሚው የግብ ክልል ቢደርስም የተሳኩ የግብ ሙከራዎችን ማድረግ ሳይችል ቀርቷል። በአንጻሩ ደግሞ በመከላከል ላይ ያመዘነ እንቅስቃሴ ያደረጉት ብሩንዲዎች በመልሶ ማጥቃት ጊዜ ግቦችን ማስቆጠር ችለዋል።


ጨዋታውን በስታዲየም ተገኝተው የተከታተሉ ተመልካቾች አሰልጣኝ አጥናፉ አለሙ ልምድ የሌላቸውን ታዳጊ ተጫዋቾች መምረጥ የሚችሉበትን እድል አለመጠቀማቸውን ተችተዋል። በተለይም በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሚገኙ ክለቦች ውስጥ የሚጫወቱ ከ20 አመት በታች የሆናቸው ተጫዋች በብዛት በሚገኙበት ሁኔታ አሰልጣኙ እድሉን አለመጠቀማቸው ለሽንፈት እንደዳረጋቸው ነው የሚገልጹት።


‹‹ተጫዋቾቼ የሚችሉትን አድርገዋል። ለሽንፈቱ ሀላፊነቱን እወስዳለሁ›› ያሉት አሰልጣኝ አጥናፉ አለሙ ግን ቡድናቸው ለደረሰበት ሽንፈት ተጋጣሚያቸው ከእድሜ በላይ ተጫዋቾችን ያካተተ በመሆኑ ነው ብለዋል።


‹‹ከጨዋታው በፊት ልምምድ ላይ የምናያቸው ነገሮች ነበሩ። በእድሜ ደረጃ ያለው የጎላ ልዩነት ግልጽ ነበር። የእኛ ተጫዋቾች በእድሜ ደረጃ ተፈትነው ወይም በዶክተሮች ተመርምረው የመጡ ናቸው። በአቅምና በፊዚካል ተበልጠናል። ይህ ደግሞ በውጤቱ ላይ ልተጽእኖ ፈጥሯል።›› ብለዋል።


የብሩንዲው አሰልጣኝ ጆስሊን ቢፕፉቡሳ ግን ተጫዋቾቻቸው ከእድሜ በላይ ናቸው የሚለውን ወቀሳ አልተቀበሉም። የቡድናቸው ተጫዋቾች አካላዊ ገጽታ ግዙፍነት ተፈጥሯቸው እንደሆነ ነው የተናገሩት።


‹‹ተጨዋቾቼ ከ20 አመት በታች ናቸው። የባሀሪ አካባቢ ወጣቶች በተፈጥሯቸው ግዙፍ ናቸው። የአየር ሁኔታውም ይመቻቸዋል። ወጣቶቹ በሙሉ ከእድሜያቸው በላይ ትልቅ የሚመስሉ ናቸው። በአካል ብቃት በታክቲክና ቴክኒክ ላይ ስንዘጋጅ ነበር።››


አሰልጣኝ ጆስሊፊን የኢትዮጵያን ቡድን ያሸነፉት በጨዋታ ታክቲክ በመብለጣቸው እንደሆነ ነው የተናገሩት። ‹‹ተጋጣሚያችን አጫጭር ኳስ የሚጫወትና ወደ ተቃራኒ ቡድን ቶሎ ቶሎ የሚመጣና የሚያጠቃ መሆኑን በማወቃችን እኛ ደግሞ በመልሶ ማጥቃት ለመጫወት ወሰንን። እንዳሰብነውም ተሳክቶልናል።›› ብለዋል።
የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ ከሶስት ሳምንት በኋላ አፕሪል 21 ቀን በንጎዚ ከተማ በስታድ ኡሩኩንዶ ይደረጋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
67 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 478 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us