ሉሲዎቹ ግብጽ ላይ የመንን ይገጥማሉ

Wednesday, 04 April 2018 13:58

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን (ሉሲ) የፊታችን ረቡዕ የመንን በግብጽ ካይሮ ላይ ይገጥማሉ። ቡድኑ የረጅም ጊዜ ልምድ ያላትን አማካይ አጥቂዋን ብርቱካን ገብረክርስቶስን በመጨረሻ ሰአት በማካተት ጠንካራ ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል።


ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከአንድ ወር በፊት የተሰባሰበው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታውን ልየመን ጋር ያደርጋል። በፖለቲካ ቀውስ ውስጥ በምትገኘው ሀገራቸው አለመረጋጋት የተነሳ በሜዳቸው የሚያደርጉትን ጨዋታ ማከናወን ያልቻሉት የመንዎች ለጨዋታው የግብጽን ሜዳ መርጠዋል።


የቅዱስ ጊዮርጊስ የሴቶች ክለብ አሰልጣኝ በሆነችው ሰላም ዘርአይ የሚመራው የሉሲዎቹ ስብስብ በፕሪሚየር ሊጉ የመጫወት ልምድ ያላቸውንና ታዳጊዎች ከብሔራዊ ማሰልጠኛ አካዳሚም ሰልጣኞችን በማካተት የተገነባ ነው። ቡድኑ በማሰልጠኛ አካዳሚ ተሰባስቦ ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቶ ባለፈው እሁድ ሽኝት ተደርጎለታል።


የሉሲዎቹ ስብስብ ለየመንው ጨዋታ ጥሩ ዝግጅት ቢያደርግም ወቅታዊ አቋሙን የሚፈትሽበት የወዳጅነት ጨዋታ አለማድረጉ ክፍተቱን ለማየት አልቻለም። ይሁንና ቡድኑ ካለው የተጫዋቾች ስብስብና ተጋጣሚውም በአፍሪካ ዝቅተኛ ደረጃ ያለው ቡድን ከመሆኑ አንጻር የመጀመሪያ ጨዋታውን በድል እንደሚወጣ ይጠበቃል።
ምንም አይነት የሴቶች ውድድር ከማይደረግበት የመን የተሰባሰበው ቡድን የጥቂት ጊዜ የጨዋታ ልምድ ያላቸው ወጣቶች ይገኙበታል። ቡድኑ በግብጽ ካይሮ ከተማ ዝግጅቱን ሲያደርግ መቆየቱን ጨዋታውን ለማስተላለፍ በስፍራው የሚገኘው ዳግም ዝናቡ ዘግቧል።
የመን በሴቶች እግር ኳስ ታሪክ የጥቂት አመታት እድሜ ያስቆጠረች ሀገር ናት። የየመን የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በአለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) እውቅናም ሆነ የእግር ኳስ ደረጃም ያልተሰጠው ነው። ቡድኑ እንደ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጨዋታ ልምድ ያላቸውና በአለምአቀፍ የውድድር መድረኮች የመጫወት ተሞክሮ የለውም። ይሁንና ቡድኑ ከፍተኛ የማሸነፍ ፍላጎት ያላቸው ተጫዋቾችን ያካተተ በመሆኑ ለኢትዮጵያ ጠንካራ ተፎካካሪ እንደሚሆን ተገምቷል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
66 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 935 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us