የዛማሌክ አሰልጣኝ በፈቃዳቸው ለቀቁ

Wednesday, 11 April 2018 14:59

በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ በኢትዮጵያዊው ክለብ ወላይታ ዲቻ ከውድድሩ ውጭ የሆነው ዛማሌክ ክለብ አሰልጣኝ ኢሀብ ሃላል በፈቃዳቸው ሀላፊነታቸውን መልቀቃቸውን አሳወቁ በሀገር ውስጥም በአፍሪካም መድረክ ውጤት ማጣቱ ለመልቀቃቸው ምክንያት ሆኗል። 

 

በዛማሌክ የእግር ኳስ ታሪክ ያልተጠበቀ እና አነስተኛ የሚባለው አህጉራዊ ውጤት በቅርቡ መመዝገቡ መነጋገሪያ እንደነበር ይታወሳል። ዛማሌክ በዘንድሮው የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ በመጀመሪያው ዙር በወላይታ ዲቻ በነበረው የደርሶ መልስ ጨዋታ ተሸንፎ ከውድድሩ መድረክ መሰናበቱ ደጋፊዎቹን ክፉኛ አሳዝኖና አስቆጥቷል። ባለፈው እሁድም ክለቡ በግብጽ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛነት ደረጃን ያጣበትን ሽንፈት አስተናግዷል። ይህም አሰልጣኙ በክለቡ የመቆየታቸውን ህልውና አደጋ ውስጥ በመክተቱ ከካይሮው ሀያል ክለብ ጋር ለመለያየት ወስነዋል።


ከአራት ወራት በፊት ዛማሌክን ማሰልጠን የጀመሩት አሰልጣኝ ሀላል ክለቡ በሀገር ውስጥ ሊግም ሆነ በአህጉራዊ መድረኮች ውጤታማ ማድረግ ባለመቻላቸው በደጋፊዎች ዘንድ ትችቶችን አስተናደዋል። በግብጽ ሊግ አልአህሊ ዋንጫ ማንሳቱን አስቀድሞ ያረጋገጠ ሲሆን፤ ዛማሌክ በቀጣዩ አመት በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊ ለመሆን የሚያስችለውን ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ለመሆን ነበር ሲፎካከር የቆየው።


ይሁንና ክለቡ በመጨረሻው የሊጉ ጨዋታ ያስመዘገበው ውጤት ደጋፊዎቹን አንገት የሚያስደፋ ነበር። አሰልጣኙም ከሀላፊነታቸው ለመልቀቅ እንዲወስኑ አድርጓል። ግብጻዊው አሰልጣኝ በካይሮው ክለብ በነበራቸው ቆይታ 16 ጨዋታዎችን አድርገዋል። ከ14 የሊግ ጨዋታዎች ሰባቱን ብቻ አሸንፈዋል። በሁለት የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የደርሶ መልስ ጨዋታ በወላይታ ዲቻ ተሸንፈው ወደ ቀጣዩ ዙር ሳያልፉ ቀርተዋል።


ዛማሌክ በሐዋሳ ስታዲየም 2ለ1 ከተሸነፈ በኋላ የመልስ ጨዋታውን በሰፊ የግብ ልዩነት እናሸንፋለን ሲሉ አሰልጣኙ ሃላል በእርግጠኝነት ተናግረው ነበር። ይሁንና የካይሮው የመልስ ጨዋታ በዛማሌክ 2ለ1 አሸማፊነት ተጠናቆ ሁለቱን ክለቦች እኩል በማድረጉ ወደ መለያ ምት ለማምራት ነበር የተገደዱት። በመለያ ምትም ወላይታ ዲቻ 5ለ4 አሸንፎ ወደ ቀጣየ ዙር ማለፍ ችሏል። ውጤቱ ለዲቻ ታላቅ ድል፤ ለዛማሌክ ደግሞ አሳፋሪ ሽንፈት ሆኖ ተጠቅሷል።


ባለፈው እሁድ በግብጽ ሊግ ዛማሌክ በማካሳ ክለብ 1ለ0 ተሸንፎ በሊጉ የሁለተኛነት እድል የሚያገኙበትን እድል አጥቷል። ከጨዋታው በኋላ አሰልጣኙ ሀላል ክለቡን በፈቃዳቸው ለመልቀቅ መወሰናቸውን ተናግረዋል። ክለቡም መልቀቂያቸውን ተቀብሎ በማሰናበት አዲስ የውጭ ሀገር ዜግነት ያለው አሰልጣኝ እንደሚቀጥር ፕሬዝዳንቱ መንሱር ማትዱር ተተናግረዋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
61 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 507 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us