ሚስቱን በእግር ኳስ ጨዋታ ያስረከበው አፍሪካዊ

Wednesday, 11 April 2018 14:50

በእግር ኳስ ጨዋታ የገንዘብ ውርርድ የተለመደ ቢሆንም አልፎ አልፎ አስገራሚ የሚባሉ ታሪኮች መሰማታቸው አልቀረም። ከገንዘብ በተጨማሪ ሀብትና ንብረትም ከፍ ሲልም ሰሞኑን ከወደ ምስራቅ አፍሪካዋ ሀገር ከታንዛኒያ የተሰማው ግን ፈጽሞ ያልተለመደና አስገራሚ ሆኗል።

 

ባለፈው ሳምንት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የማንቸስተር ደርቢ ጨዋታ ብዙ የእግር ኳስ አፍቃሪዎች የተመለከቱትና የተወራረዱበትም ነበር። በታንዛኒያም ከጨዋታው በፊትም ሁለት ደጋፊዎች ለመወራረድ ይስማማሉ። ውርርዳቸው ደግሞ በገንዘብ ወይም በንብረት አልነበረም። በሌላ ሰው ህይወት፤ በሚስቶቻቸው ነበር። ቡድኑ የተሸነፈበት ወገን ሚስቱን ለሌላኛው ለአንድ ሳምንት ለመስጠት እንደሚፈቅድ የስምምነታቸው ወረቀት ይገልጻል። ይህንንም ስምምነት ሁለቱም ግለሰቦች በእጅ ጽሑፍ አስፍረው ፊርማቸውን በማኖር ለእማኞች አስረክበዋል።


በኢትሃድ የተካሔደውን የማንቸስተር ደርቢ ጨዋታ ውጤት ብዙዎች በጉጉት የሚጠብቁት ቢሆንም ሚስቶቻቸውን ለውርርድ ያቀረቡት ቶኒ ሺላ እና አማኒ ስታንሌይ ግን ልዩ ነበር። ጨዋታውም በማንቸስተር ዩናይትድ አሸናፊነት ተጠናቀቀ። ውጤቱ የጆዜ ሞሪሆን ስም እንደገና ያገነነ ነበር። ጋርዲዮላንና የሲቲ ደጋፊዎችን ደግሞ እጅግ ያሳዘነ ክስተት ሆነ። ከምንም በላይ ግን ውጤቱ ለአማኒ ስታንሌይ የከፋ ነበር። አስቀድሞ ለውርርድ በሰጠው ቃሉ መሰረት የሚወዳት ሚስቱን አሳልፎ ማስረከብ ይኖርበታል።


እንደ ኬንያው ናይሮቢ ኒውስ ዘገባ ከሆነ በሁለቱ አባወራዎች መካከል የተፈጸመው ስምምነት ተፈጻሚ የመሆኑ ጉዳይ አልታወቀም።


ከዚህ በፊት አስገራሚ የውርርድ አይነቶች ተፈጽመው ያውቃሉ። ለአብነት ያህልም በ2013 ማንቸስተር ዩናይትድና አርሴናል ጨዋታ ኡጋንዳውያን የፈጸሙት የውርርድ አይነት አንደኛው ነው። የአርሴናሉ ደጋፊ ቤቱን ነበር ለውርርድ ያቀረበው። የማንቸስተር ዩናይትዱ ደጋፊ ደግሞ ቶዮታ መኪናውንና ሚስቱን አቀረበ። ጨዋታው በዩናይትድ 1ለ0 እንደተጠናቀቀም የዩናይትድ ደጋፊ የሆኑ ወደ አርሴናሉ ደጋፊ ቤት በመሔድ ሶስት ሚስቶቹንና ልጆችን ከቤቱ ጎትተው በማውጣት ከፍተኛ ድብደባ መፈጸማቸው ይታወሳል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
78 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 542 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us