ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ወደ ብሩንዲ ያቀናል

Wednesday, 11 April 2018 15:05


የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ወንዶች ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን ቡጅንቡራ ከተማ ላይ በብሩንዲ አስተናጋጅነት ከሚያዚያ 6 እስከ 20/2010 ዓ.ም ለሚካሄደው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ቻሌንጅ ካኘ ውድድር ዛሬ ይጓዛል።

 

 በዋና አሰልጣኝ ተመስገን ዳና የሚመራው ቡድን ከመጋቢት 12 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ልምምዱን በማድረግ የተወሰኑ የአቋም መለኪያ ጨዋታዎችን ያደረገ ሲሆን ሚያዚያ 6 ቀን በሚደረገው የመጀመሪያ የመክፈቻ ጨዋታው የሱማሊያ አቻውን ይገጥማል።


በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ከ17 ዓመት በታች የታዳጊዎች ውድድር አገራችን ኢትዮጵያ በዓይነቱ የመጀመሪያ ተሳተፎዋ ቢሆንም ተተኪዎችን ለማፍራት ፌዴሬሽኑ እየሰራበት ለሚገኘው የኘሪሚየር ሊግ ታዳጊዎች እና ወጣቶች ውድድር ተሳታፊ ለሆኑ ተጨዋቾች የኢንተርናሽናል ልምድ ለመቅሰም መልካም ግብአት እንደሚሆን ይጠበቃል።


አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለጸው 20 ተጫዋቾችን ይዞ ወደ ቦታው እንደሚያቀና ገልጾ ‹‹ሁሉም ተጫዋቾች በሙሉ ጤንነት ላይ ስለሚገኙ ወደ ስፍራው የምናቀናው ለዋጫ ነው›› ብሏል፡፡ ከ25 ቀናት ያልበለጠ ጊዜ መዘጋጀታቸውንም አሰልጣኙ ጨምሮ ተናግሯል፡፡ ‹‹ዋናው የቡድኑ ዓላማም ለአፍሪካ ከ17 ዓት በታች ዋንጫ ማለፍ ነው›› ሲል ተናግሯል፡፡


አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ከዚህ በፊት በሐዋሳ ከነማ ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ቡድን አሰልጣኝነት ውጤታማነቱን ያስመሰከረ ወጣት አሰልጣኝ ሲሆን፤ ያለፈው ዓመት የውድድሩ ኮከብ አሰልጣኝ ተብሎ መመረጡም ይታወሳል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
91 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 709 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us