ፕሪሚየር ሊጉ በድጋሚ ቀጥሏል

Wednesday, 16 May 2018 13:32

የኢትዮጰያ ፕሪሚየር ሊግ በመከላከያና ወልዋሎ ጨዋታ አቢርትር እያሱ ፈንቴ ላይ ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰኞ እለት በድጋሚ እንዲጀምር ተደርጓል። የኢትዮጵያ ዳኞችና ታዛቢዎች ማህበር ጨዋታዎችን ለመምራት ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች እንደሚሟሉ ከፌዴሬሽኑ ጋር ባደረገው ስምምነት በመገለጹ ነበር ሊጉ እንዲቀጥል የተደረገው።


ፕሪሚየር ሊጉ ሰኞ እለት በድጋሚ ሲቀጥል በአዲስ አበባ ስታዲየም ቅዱስ ጊዮርጊስና ኤሌትሪክ፤ በአዳማ ደግሞ አዳማ ከተማ ከወላይታ ዲቻ ጋር ተጫውተዋል። ከመሪዎቹ ተርታ የሚገኙት ቅዱስ ጊዮርጊስና አዳማ ተጋጣሚያቸውን በማሸነፍ ሶስት ነጥብ ማግኘት ችለዋል።


በአዲስ አበባ ስታዲየም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመሪዎቹ ተርታ እንዲሰለፍ ያደረገውን የ2ለ1 ውጤት አስመዝግቧል።


የሊጉ መርሀግብር በቀጣይ አርብ ቀን ሁለት ጨዋታዎችን በማስተናገድ ይከናወናል። ድሬደዋ ላይ ድሬደዋ ከተማ ወላይታ ዲቻን ያስተናግዳል። ድሬደዋ ከተማ ከወራጅ ቀጠናው ለመውጣት በሜዳውና ደጋፊው ፊት የሚያርገውን ጨዋታ ለማሸነፍ ከፍተኛ ተጋድሎ እንደሚያደርግ ይጠበቃል። ክለቡ ጨዋታውን ማሸነፍ ከቻለ ነጥቡን ወደ 22 በማሳደግ በተመሳሳይ ነጥብ ላይ የሚገኘውን አርባምንጭ ከተማ በግብ ክፍያ በመብለጥ የ11ኛነት ደረጃን ይረከበዋል።


በተመሳሳይ ቀንና ሰአት በትግራይ ስታዲየም ደግሞ መቀሌ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን ይገጥማል። ጨዋታው ሁለቱ ክለቦች ለሻምፒዮናነት ለሚያደርጉት ጉዞ ወሳኝ በመሆኑ ከፍተኛ ፉክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። ጊዮርጊስ የሁለተኘነት ደረጃውን ለማስጠበቅ፤ መቀሌ ከተማም አሸንፎ የሁለተኛነት ደረጃን ለመያዝ ይጫወታሉ።


ፕሪሚየር ሊጉን ጅማ አባጅፋር በ22 ጨዋታዎች 39 ነጥብ ይዞ በአንደኛነት እየመራ ነው። ጊዮርጊስ በ21 ጨዋታዎች 36 ነጥቦችን በመሰብሰብ ሁለተኛ ሲሆን፤ መቀሌ ከተማ በ20 ጨዋታዎች 35 ነጥብ ይዞ አዳማ ከተማን በመከተል አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
44 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 464 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us