መሐመድ ሳላህ ሮናልዶና አለን ሺረርን በልጦ ተሸልሟል

Wednesday, 16 May 2018 13:33

 

ግብጻዊው የሊቨርፑል አጥቂ መሐመድ ሳላህ የዘንድሮውን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክስተት ሆኖ አመቱን አጠናቋል። ተጨዋቹ በፕሪሚየር ሊጉ በርካታ ክብረወሰኖችን በማስመዝገብ አድናቆትን አትርፏል። የውድድር አመቱም ክርስቲያኖ ሮናልዶና አለን ሺረር ያስመዘገቡትን ክብረወሰን በማሻሻል ልቋቸው ተገኝቷል።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ሲጠናቀቅ መሀመድ ሳላህ በሊቨርፑል የአመቱ የመጨረሻ ጨዋታ ላይ አንድ ግብ ማስቆጠር ችሏል። ግቧም በፕሪሚየር ሊጉ በአንድ የውድድር ዘመን ብዙ ግቦችን በማስቆጠር ክብረወሰን ይዘው የነበሩትን ክርስቲያኖ ሮናልዶና አለን ሺረርን በልጦ እንዲገኝ አስችላዋለች። የዘንድሮው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ አግቢ ተሸላሚም አድርጋዋለች።
ክርስቲያኖ ሮናልዶና አለን ሺረር በአንድ የውድድር ዘመን በእንግሊዝ ያስመዘገቧው ግቦች 31 ነበሩ። እሁድ እለት ሳላህ አንድ ግብ በማስቆጠር የግቡን ብዛተ 32 አድርሷ። ሮናለዶና ሺረርን ክብረወሰን በስሙ ማስመዝገብ ችሏል።
የ2017 የአፍሪካ ኮከብ ተጨዋች በቀጣዩ የ2018 የአለም ዋንጫ ከሚጠበቁ ተጨዋቾች መካከል አንዱ ሆኗል። ግብጽ ለአለም ዋንጫው እንድታልፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉ ይታወቃል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
45 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 546 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us